ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ! ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፤ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች!
ሆሴዕ 2:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አለበለዚያ ዕራቁትዋን እንድትሆን እገፍፋታለሁ፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን አደርጋታለሁ፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር አደርጋታለሁ፥ በጥምም እገድላታለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እናታቸው አመንዝራ ናት፤ በውርደትም ፀንሳቸዋለች፤ እርሷም፣ ‘እንጀራዬንና ውሃዬን ይሰጡኛል፤ ሱፌንና የሐር ልብሴን፣ ዘይቴንና መጠጤን ይሰጡኛል፤ ስለዚህ ውሽሞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ’ አለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናታቸው አመንዝራ ስለ ሆነች እነርሱን ባሳፋሪ መንገድ ፀንሳቸዋለች፤ እርስዋም ይህን ያደረገችው ምግቤንና ውሃዬን፥ የሱፍና የተልባ እግር ልብሴን፥ ዘይቴንና መጠጤን የሚሰጡኝ ስለ ሆነ ፍቅረኞቼን ተከትዬ እሄዳለሁ ብላ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እናታቸው አመንዝራለችና፤ የወለደቻቸውም፥ “እንጀራዬንና ውኃዬን፥ ቀሚሴንና መደረቢያዬን፥ ዘይቴንና የሚገባኝን ሁሉ የሚሰጡኝ ወዳጆችን እከተላቸው ዘንድ እሄዳለሁ” ብላለችና አሳፈረቻቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዕራቁትዋን እንዳልገፍፋት፥ እንደ ተወለደችበትም ቀን እንዳላደርጋት፥ እንደ ምድረ በዳና እንደ ደረቅ ምድር እንዳላደርጋት፥ |
ታማኝ የነበረችው ከተማ እንዴት አመንዝራ እንደ ሆነች ተመልከቱ! ቀድሞ ፍትሕ የሞላባት፤ ጽድቅ የሰፈነባት ነበረች፤ አሁን ግን የነፍሰ ገዳዮች ማደሪያ ሆነች!
ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናታችሁን የፈታሁበት የፍቺዋ ጽሕፈት የት አለ? ወይስ እናንተን የሸጥሁ ከአበዳሪዎች ለየትኛው ነው? እነሆ፥ ስለ ኃጢአታችሁ ተሸጣችኋል፥ ስለ በደላችሁም እናታችሁ ተፈታለች።
ይሁዳ ሆይ! አማልክትህ እንደ ከተሞችህ ቍጥር እንዲሁ ናቸው፤ እንደ ኢየሩሳሌምም መንገዶች ቍጥር ለአሳፋሪ ነገር መሠዊያዎችን ሠርታችኋል፥ እነርሱም ለበዓል የምታጥኑባቸው መሠዊያዎች ናቸው።
“ከጥንት ጀምሮ ቀንበርሽን ሰብረሻል እስራትሽንም በጥሰሻል፤ አንቺም፦ ‘አላገለግልም’ አልሽ፥ ነገር ግን ከፍ ባለው ኮረብታ ሁሉ ላይ ከለምለምም ዛፍ ሁሉ በታች ለማመንዘር ተጋደምሽ።
በእጃቸውም አሳልፌ እሰጥሻለሁ፥ ጉብታሽን ያፈርሳሉ፥ ከፍ ያለውንም ቦታሽን ይገለብጣሉ፤ ልብሶችሽንም ይገፉሻል፥ የሚያምሩ ጌጣጌጦችሽን ይወስዳሉ፥ ዕርቃንሽንና ዕራቁትሽን ይተዉሻል።
ስትወለጂ፥ በተወለድሽበት በዚያው ቀን እትብትሽ አልተቆረጠም ነበር፥ ንጹሕም እንድትሆኚ በውኃ አልታጠብሽም፥ በጨው አልታሸሽም፥ በጨርቅም አልተጠቀለልሽም።
ጌታ መጀመሪያ በሆሴዕ በተናገረ ጊዜ፥ ጌታ ሆሴዕን፦ “ምድሪቱ ከጌታ ርቃ ታላቅ ዝሙት አድርጋለችና ሂድ፤ አመንዝራን ሴት ውሰድና አግባ፤ የዝሙትም ልጆች ይኑሩህ፥” አለው።
የይሁዳ ልጆችና የእስራኤል ልጆች በአንድነት ይሰበሰባሉ፥ እነርሱም አንድ አለቃ በራሳቸው ላይ ይሾማሉ፤ የኢይዝራኤልም ቀን ታላቅ ይሆናልና ከምድሪቱ ይወጣሉ።
ጌታም እንዲህ አለኝ፦ “የእስራኤል ልጆች ወደ ሌሎች አማልክት ቢመለሱና የዘቢብ ጥፍጥፍን ቢወድዱ እንኳ ጌታ እንደሚወድዳቸው እንዲሁ አንተም ዳግመኛ ሂድ፥ በውሽማዋ የምትወደደውን አመንዝራይትን ሴት ውደድ።”
እስራኤልን በምድረ በዳ እንዳለ እንደ ወይን ዘለላ ሆኖ አገኘሁት፤ አባቶቻችሁንም በወቅቱ መጀመሪያ ላይ እንዳለ እንደ በለስ በኵራት በበለስ ዛፍ ላይ ሆነው አየኋቸው፤ እነርሱ ግን ወደ ባዓል-ፌዖር መጡ፥ ለእፍረትም ነገር ራሳቸውን ለዩ፥ እንደ ወደዱትም ርኩስ ሆኑ፥
በዚህ ጊዜ የፍልስጥኤማውያን ገዦች፥ “አምላካችን ዳጎን፥ ጠላታችን ሳምሶንን በእጃችን አሳልፎ ሰጥቶናል” ብለው በመደሰት ለአምላካቸው ለዳጎን ታላቅ መሥዋዕት ለማቅረብ ተሰበሰቡ።