ዕብራውያን 9:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ሲሆን፥ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም የማያደርጉ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህም ለአሁኑ ዘመን ምሳሌ ሲሆን፣ የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የሚያመልከውን ሰው ኅሊና ፍጹም ሊያደርጉ አልቻሉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፤ በዚህ ዐይነት የሚቀርቡት መባና መሥዋዕት የአቅራቢውን ሰው ኅሊና ፈጽመው ሊያነጹት አይችሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ለሚያቀርበው ሰው ግዳጅ መፈጸም የማይቻለውን መባና መሥዋዕት ያቀርቡበት የነበረው ለዚህ ዘመን ምሳሌ ሆነ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ይህም ለአሁኑ ጊዜ ምሳሌ ነው፥ እንደዚህም መባና መስዋዕት ይቀርባሉ፤ እነዚህም እስከ መታደስ ዘመን ድረስ የተደረጉ፥ ስለ ምግብና ስለ መጠጥም ስለ ልዩ ልዩ መታጠብም የሚሆኑ የሥጋ ሥርዓቶች ብቻ ናቸውና የሚያመልከውን በህሊና ፍጹም ሊያደርጉት አይችሉም። |
እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤
እንግዲህ በሌዊ ክህነት ፍጹምነት የተገኘ ከሆነ፥ ሕዝቡ በዚያ ላይ የተመሠረተን ሕግ ተቀብለዋልና፤ ወደ ፊት እንደ አሮን ሹመት የሚቆጠር ሳይሆን፥ እንደ መልከጼዴቅ ሹመት የሆነ ሌላ ካህን ሊነሣ ስለምን ያስፈልጋል?
ክርስቶስ በእጅ ወደ ተሠራች፥ የእውነተኛይቱ ምሳሌ ወደምትሆን ቅድስት አልገባም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር ፊት ስለ እኛ አሁን ለመታየት ወደ እርሷ ወደ ሰማይ ገባ።
ይህ ውሃ አሁን የጥምቀት ምሳሌ ሆኖ እናንተን ያድናል፤ የሰውነትን እድፍ ማስወገድ ሳይሆን፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ፥ ለእግዚአብሔር የሚቀርብ የበጎ ሕሊና ልመና ነው።