ዕብራውያን 9:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተመሳሳይ በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጭቷል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም ድንኳኒቱንና ማገልገያ ዕቃውን ሁሉ በደም ረጨው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በድንኳኒቱና በመገልገያ ዕቃ ሁሉ ላይ ደምን ረጨ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ድንኳኑንና የመገልገያውን ዕቃ ሁሉ በደሙ ይረጭ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁም በድንኳኒቱና በማገልገያው ዕቃ ሁሉ ደምን ረጨ። |
አውራውን በግ አርደህ ደሙን ትወስዳለህ፥ የአሮንንም የቀኝ ጆሮ ጫፍ፥ የልጆቹንም የቀኝ ጆሮአቸውን ጫፍ፥ የቀኝ እጃቸውንና የቀኝ እግራቸውን አውራ ጣት ታስነካለህ፤ ደሙንም በመሠዊያው ላይ ዙሪያውን ትረጨዋለህ።
ለማስተስረያ የሚሆን የኃጢአት መሥዋዕት ወይፈን በየቀኑ ታቀርባለህ፤ በእርሱ ላይ ማስተስረያ በምታደርግበት ጊዜ መሠዊያውንም ታስተሰርይለታልህ፤ ቅዱስም እንዲሆን ትቀባዋለህ።
አረደውም፤ ሙሴም ደሙን ወስዶ በጣቱ የመሠዊያውን ቀንዶች ዙሪያ ቀባ፥ መሠዊያውንም አነጻው፤ ደሙንም ከመሠዊያው በታች አፈሰሰው፥ እንዲያስተሰርይለትም ቀደሰው።
ስለ ሕዝቡ የአንድነት መሥዋዕት የሚቀርበውን በሬውንና አውራውን በግ አረደ፤ የአሮንም ልጆች ደሙን አመጡለት፥ በመሠዊያውም ላይ በዙሪያው ረጨው፤