“ለሕዝቡም የሆነውን የኃጢአት መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፥ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ እንዲሁ በፍየሉ ደም ላይ ያደርጋል፤ በስርየቱ መክደኛም ላይና በስርየቱ መክደኛም ፊት ለፈት ይረጨዋል።
ዕብራውያን 5:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለ ራሱ ኀጢአትና ስለ ሌሎች ሰዎች ኀጢአት መሥዋዕት ማቅረብ የተገባው በዚሁ ምክንያት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱ ራሱም በደካማነቱ ምክንያት የኃጢአት ይቅርታን የሚያስገኝ መሥዋዕትን ማቅረብ የሚገባው ለሕዝቡ ብቻ ሳይሆን ለራሱም ጭምር ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መሥዋዕትን ስለ ኀጢአት ማቅረብ ይገባዋል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚህም ምክንያት ስለ ሕዝብ እንደሚያቀርብ እንዲሁ ስለ ራሱ ደግሞ መስዋዕትን ስለ ኃጢአት ሊያቀርብ ይገባዋል። |
“ለሕዝቡም የሆነውን የኃጢአት መሥዋዕት ፍየል ያርዳል፥ ደሙንም ወደ መጋረጃው ውስጥ ያመጣዋል፤ በወይፈኑም ደም እንዳደረገ እንዲሁ በፍየሉ ደም ላይ ያደርጋል፤ በስርየቱ መክደኛም ላይና በስርየቱ መክደኛም ፊት ለፈት ይረጨዋል።
ሙሴም አሮንን፦ “ወደ መሠዊያው ቅረብ፥ የኃጢአትህንም መሥዋዕትና የሚቃጠለውን መሥዋዕትህን ሠዋ፥ ለራስህና ለሕዝቡም አስተስርይ፤ ጌታም እንዳዘዘ የሕዝቡን ቁርባን አቅርብ አስተስርይላቸውም” አለው።
እርሱ እንደነዚያ ሊቃነ ካህናት፥ አስቀድሞ ስለ ራሱ ኃጢአት በኋላም ስለ ሕዝቡ ኃጢአት፥ ዕለት ዕለት መሥዋዕትን ማቅረብ አያስፈልገውም፤ ይህን ራሱን ባቀረበ ጊዜ አንድ ጊዜ ፈጽሞ አድርጎታል።
በሁለተኛይቱ ግን ሊቀ ካህናት ብቻውን በዓመት አንድ ጊዜ ይገባባታል፤ እርሱም ሰለ ራሱና ስለ ሕዝቡ ኃጢአት የሚያቀርበውን ደም ሳይዝ አይገባም፤