ዕብራውያን 3:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ካልታዘዙትም በስተቀር፥ ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ? አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ደግሞስ እነዚያን ያልታዘዙትን ካልሆነ በቀር “ወደ ዕረፍቴ አትገቡም” ብሎ የማለባቸው እነማን ነበሩ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከካዱት በቀር ወደ ዕረፍቱ እንዳይገቡ በማን ላይ ማለ? መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካልታዘዙትም በቀር ወደ እረፍቱ እንዳይገቡ የማለባቸው እነማን ነበሩ? |
ጌታም ሙሴን እንዲህ አለው፦ “ይህ ሕዝብ እስከ መቼ ይንቀኛል? በመካከላቸውም ስላደረግሁት ተአምራት ሁሉ እንኳ እስከ መቼ ድረስ በእኔ አያምኑም?
ጌታም ሙሴንና አሮንን እንዲህ አላቸው፦ “በእስራኤል ልጆች ፊት ቅድስናዬን ለማሳየት በእኔ አላመናችሁምና ስለዚህ ወደ ሰጠኋቸው ምድር ይህን ጉባኤ ይዛችሁ አትገቡም።”
ጌታም፥ ‘ውጡ የሰጠኋችሁንም ምድር ውረሱ’ ብሎ ከቃዴስ በርኔ በላካችሁ ጊዜ፥ በጌታ በአምላካችሁ ቃል ላይ ዐመፃችሁ፥ በእርሱም አላመናችሁም፥ ለቃሉም አልታዛችሁም።