ዕብራውያን 13:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፤ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ ታውቁ ዘንድ እፈልጋለሁ፤ ቶሎ ከመጣ፣ ከርሱ ጋራ ላያችሁ እመጣለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወንድማችን ጢሞቴዎስ ከእስር ቤት እንደ ወጣ እንድታውቁ እወዳለሁ፤ በቶሎ ወደዚህ ከመጣ ከእርሱ ጋር ወደ እናንተ መጥቼ አያችኋለሁ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድማችን ጢሞቴዎስ ከእኛ ወደ እናንተ እንደ ተላከ ዕወቁ፤ ፈጥኖ ከመጣ አያችኋለሁ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወንድማችን ጢሞቴዎስ እንደ ተፈታ እወቁ፥ ቶሎ ብሎም ቢመጣ ከእርሱ ጋር አያችኋለሁ። |
ስለ እምነታችሁም እንዲያጸናችሁና እንዲመክራችሁ ወንድማችንን፥ የእግዚአብሔርንም አገልጋይ ከእኛ ጋርም አብሮ በክርስቶስ ወንጌል የሚሠራውን ጢሞቴዎስን ላክነው፤
እንግዲህ ስለ ጌታችን ምስክርነት በመስጠት ወይም ስለ እርሱ በታሰርሁ በእኔ አትፈር ይልቁንም እንደ እግዚአብሔር ኃይል መጠን ስለ ወንጌል አብረኸኝ መከራን ተቀበል።
እኔም “ጌታ ሆይ! አንተ ታውቃለህ፤” አልሁት። እንዲህም አለኝም፦ “እነዚህ ከታላቁ መከራ የመጡ ናቸው፤ ልብሶቻቸውንም አጥበው በበጉ ደም አንጽተዋል።