ዕብራውያን 12:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፥ ወደ ጭጋጉና ወደ ጨለማው፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱ ገና አልደረሳችሁም፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሊዳሰስ ወደሚችለውና በእሳት ወደሚቃጠለው ተራራ፣ ወደ ጨለማው፣ ወደ ጭጋጉና ወደ ዐውሎ ነፋሱ አልደረሳችሁም፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እናንተ በእጅ ወደሚዳሰሰው ወይም ወደሚቃጠለው ወደ ሲና ተራራ አልደረሳችሁም፤ ወደ ጭጋጉ፥ ወደ ጨለማውም፥ ወደ ዐውሎ ነፋሱም፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም፥ ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም፥ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሊዳሰስ ወደሚችል ወደሚቃጠልም እሳት ወደ ጭጋግም ወደ ጨለማም ወደ ዐውሎ ነፋስም ወደ መለከት ድምፅም ወደ ቃሎችም ነገር አልደረሳችሁምና፤ |
እንደገና የፍርሃት ባርያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፥ ነገር ግን “አባ! አባት!” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋል።
ዳሩ ግን የእስራኤል ልጆች ስለዚያ ስለ ተሻረው፥ ስለ ፊተኛው ክብር የሙሴን ፊት ትኩር ብለው መመልከት እስኪሳናቸው ድረስ፥ ያ በፊደላት በድንጋዮች ላይ የተቀረጸ የሞት አገልግሎት ያን ያህል ክቡር ከሆነ፥
እናንተም ቀርባችሁ ከተራራው በታች ቆማችሁ ነበር፥ እስከ ሰማይም ድረስ እሳት በተራራው ላይ ይነድድ ነበር፥ ጨለማም ደመናና ድቅድቅ ጨለማ ነበረ።
እናንተ በእሳቱ ምክንያት ፈርታችሁ፥ ወደ ተራራውም አልወጣችሁምና፤ በዚያን ጊዜ፥ እኔ የጌታን ቃል ልነግራችሁ፥ በጌታና በእናንተ መካከል ቆሜ ነበር። እግዚአብሔርም እንዲህ አለ፦