ዕብራውያን 11:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ በቅን ፈረዱ፤ የተሰጠውን የተስፋ ቃል ተቀበሉ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፤ በፍትሕ አስተዳደሩ፤ የተሰጣቸውንም ተስፋ አገኙ፤ የአንበሶችን አፍ ዘጉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱ በእምነት ተጋደሉ፤ ነገሥታትን ድል ነሡ፤ ጽድቅን አደረጉ፤ ተስፋቸውን አገኙ፤ የአናብስትንም አፍ ዘጉ ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱ በእምነት መንግሥታትን ድል ነሡ፥ ጽድቅን አደረጉ፥ የተሰጠውን የተስፋ ቃል አገኙ፥ |
በአህያው ላይ ተቀምጦ ሄደ፤ የነቢዩንም ሬሳ አህያውና አንበሳው እስከ አሁን በአጠገቡ እንደ ቆሙ በመንገድ ላይ ተጋድሞ አገኘው። አንበሳውም የነቢዩን ሬሳ አልበላም፤ በአህያውም ላይ አደጋ አልጣለበትም ነበር።
የተስፋውም ቃል የተነገረው ለአብርሃምና ለዘሩ ነበር። ለብዙዎች እንደሆነ “ለዘሮችህ” አይልም፤ ነገር ግን ለአንድ እንደሆነ “ለዘርህም” ይላል፤ እርሱም ክርስቶስ ነው።
ነገር ግን አንድ ሰው “አንተ እምነት አለህ፤ እኔ ሥራ አለኝ” ቢል፤ እምነትህን ከሥራ ለይተህ አሳየኝ፤ እኔም እምነቴን በሥራዬ አሳይሃለሁ።