ዕብራውያን 10:9 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም “እነሆ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ፤” ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቀጥሎም፣ “እነሆኝ፤ ፈቃድህን ለማድረግ መጥቻለሁ” አለ፤ ሁለተኛውን ለመመሥረት የመጀመሪያውን ሻረ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቀጥሎም “እነሆ፥ እኔ ፈቃድህን ለመፈጸም መጥቻለሁ” አለ፤ በዚህ ሁኔታ ሁለተኛውን ዐይነት መሥዋዕት በቦታው ለመተካት የመጀመሪያውን ዐይነት መሥዋዕት ሽሮአል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዚህ በኋላ፥ “አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን አደርግ ዘንድ እነሆ፥ መጣሁ” አለ፤ ይህ ቃል የኋለኛውን ያቆም ዘንድ የፊተኛውን ያፈርሳል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቀጥሎ፦ እነሆ፥ አምላኬ ሆይ፥ ፈቃድህን ላደርግ መጥቼአለሁ ብሎአል። ሁለተኛውንም ሊያቆም የፊተኛውን ይሽራል። |