ዕብራውያን 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)8 በዚህ ላይ “መሥዋዕትንና መባን የሚቃጠል መሥዋዕትንም፥ ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም፥ በእርሱም ደስ አላለህም፤” ይላል። እነዚህም እንደ ሕጉ የሚቀርቡት ናቸው። Ver Capítuloአዲሱ መደበኛ ትርጒም8 ሕጉ ይህ እንዲደረግ ቢያዝም፣ እርሱ ግን በመጀመሪያ፣ “መሥዋዕትንና መባን፣ የሚቃጠል መሥዋዕትንና ስለ ኀጢአት የሚቀርበውን መሥዋዕት አልፈለግህም፤ ደስም አልተሠኘህበትም” ይላል። Ver Capítuloአማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም8 እሱም በመጀመሪያ እነዚያ በሕጉ መሠረት የታወጁ ቢሆኑ እንኳ “መሥዋዕትንና መባን፥ የሚቃጠለውን መሥዋዕትና ስለ ኃጢአት ስርየት የሚሠዋውን መሥዋዕት አልፈለግህም፤ በእነርሱም አልተደሰትህም” አለ፤ Ver Capítuloየአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)8 በዚህ ላይ “መሥዋዕትንና መባን፥ በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም፥ ስለ ኀጢአትም የሚሠዋ መሥዋዕትን አልወደድህም፤ በእርሱም ደስ አላለህም” ብሎ ተናገረ፤ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡ ናቸው። Ver Capítuloመጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)8 ይላል። በዚህ ላይ፦ መሥዋዕትንና መባን በሙሉ የሚቃጠል መሥዋዕትንም ስለ ኃጢአትም የሚሰዋ መሥዋዕትን አልወደድህም በእርሱም ደስ አላለህም ብሎ፥ እነዚህም እንደ ሕግ የሚቀርቡት ናቸው፥ Ver Capítulo |