ዕንባቆም 3:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በፈረሶችህ በባሕር ላይ ተራመድህ፥ ብዙ ውኆችንም ረገጥህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ታላላቅ ውሆችን በመናጥ፣ ባሕሩን በፈረሶችህ ረገጥህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንተ ባሕሩን በፈረሶችህ በምትረጋግጥበት ጊዜ ጥልቁ ባሕር ይናወጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፈረሶችህን በባሕር፥ በብዙ ውኆችም ላይ አስረገጥህ። |
ጌታ ሆይ ንዴትህ በወንዞች ላይ ነውን? ወይስ ቁጣህ በወንዞች ላይ ወይም መዓትህ በባሕር ላይ ነውን? በፈረሶችህ፥ በማዳን ሰረገሎች ላይ ተቀምጠሃልና።