La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 7:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያውም ቀን ኖኅ፥ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ወደ መርከብ ገቡ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ዕለት ኖኅና ልጆቹ ሴም፣ ካምና ያፌት፣ እንዲሁም ሚስቱና ሦስቱ የልጆቹ ሚስቶች ወደ መርከቧ ገቡ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዝናቡ መዝነብ በጀመረበት ቀን፥ ኖኅና ሚስቱ ከልጆቻቸው ከሴም፥ ከካም፥ ከያፌትና ከሦስቱም ልጆቻቸው ሚስቶች ጋር ወደ መርከቡ ገቡ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያ​ውም ቀን ኖኅ ወደ መር​ከብ ገባ፤ የኖኅ ልጆ​ችም ሴም፥ ካም፥ ያፌ​ትና የኖኅ ሚስት፥ ሦስ​ቱም የል​ጆቹ ሚስ​ቶች ከእ​ርሱ ጋር ገቡ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያውም ቀን ኖኅ ወደ መርከብ ገባ የኖኅ ልጆችም ሴም፥ ካም፥ ያፌትና የኖኅ ሚስት ሦስቱም የልጆቹ ሚስቶች ከርሱ ጋር ገቡ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 7:13
16 Referencias Cruzadas  

ለሴምም ደግሞ ልጆች ተወለዱለት፥ እርሱም የያፌት ታላቅ ወንድምና የዔቦር ልጆች ሁሉ ቅድመ አያት ነው።


የካም ልጆች፦ ኩሽ፥ ምጽራይም፥ ፉጥ እና ከነዓን ናቸው።


ኖኅም ሴምን፥ ካምን እና ያፌትን ወለደ፤ ኖኅም የአምስት መቶ ዓመት ሰው ነበረ።


ሴም፥ ካምና ያፌት የሚባሉትን ሦስት ወንዶች ልጆች ወለደ።


ከአንተ ጋር ግን ቃል ኪዳን እገባለሁ፤ አንተና ሚስትህ፥ ልጆችህና የልጆችህ ሚስቶች ይዘህ ወደ መርከቡ ትገባለህ።


ጌታም ኖኅን እንዲህ አለው፦ “በዚህ ዘመን ካለው ትውልድ መካከል ጻድቅ አንተ ሆነህ አይቼሃለሁና፥ አንተ ቤተሰቦችህን ሁሉ ይዘህ ወደ መርከብ ግባ።


ከእነርሱ ጋር፥ ከአራዊት፥ ከእንስሶች፥ በደረታቸው እየተሳቡ ከሚንቀሳቀሱ ፍጥረቶችና በሰማይ ከሚበርሩ ወፎች ከእያንዳንዱ ዓይነት አብረዋቸው ገቡ።


በሁለተኛውም ወር ከወሩም በሀያ ሰባተኛው ቀን ምድር ፈጽማ ደረቀች።


ኖኅ ገና ስለማይታየው ነገር ተረድቶ እግዚአብሔርን እየፈራ ቤተ ስዎቹን ለማዳን መርከብን በእምነት አዘጋጀ፤ በዚህም ዓለምን ኰነነ፤ በእምነትም የሚገኘውን ጽድቅ ወራሽ ሆነ።


እነዚህ ቀድሞ በኖኅ ዘመን መርከብ ሲሠራ እግዚአብሔር በትዕግሥት ሲጠብቃቸው አንታዘዝም ያሉ ናቸው። በውሃ የዳኑት ጥቂት ሲሆኑ እነርሱም ስምንት ሰዎች ብቻ ነበሩ።


ለቀደመውም ዓለም ሳይራራ፥ ጽድቅን የሚሰብከውን ኖኅን ከሌሎች ሰባት ሰዎች ጋር አድኖ፥ በኀጢአተኞች ዓለም ላይ የጥፋትን ውሃ ካወረደ፥


አባቶቻቸውም ሆኑ ወንድሞቻቸው ቢቃወሙ፥ ‘በጦርነት ጊዜ ለእያንዳንዳቸው የሚሆኑ ሚስቶች ስላላገኘን ነውና እነርሱን በመርዳት ምሕረት አድርጉልን፤ እናንተም ደግሞ ልጆቻችሁን ፈቅዳችሁ ያልዳራችሁ በመሆናችሁ በደለኞች አትሆኑም’ እንላቸዋለን።”