La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 46:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብና ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ መጡ፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ከብቶቻቸውንና በከነዓን ምድር ያፈሩትን ሀብት ንብረታቸውን ይዘው፣ ያዕቆብና ዘሮቹ በሙሉ ወደ ግብጽ ወረዱ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከብቶቻቸውንና በከነዓን ያፈሩትን ሀብት ሁሉ ይዘው ወደ ግብጽ ሄዱ፤ በዚህ ዐይነት ያዕቆብ ቤተሰቡን ሁሉ ይዞ ወደ ግብጽ ሄደ፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ጓዛ​ቸ​ውን፥ በከ​ነ​ዓን ሀገ​ርም ያገ​ኙ​ትን ጥሪ​ታ​ቸ​ውን ሁሉ ይዘው ያዕ​ቆ​ብና ዘሩ ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንስሶቻቸውንም በከነዓን አገርም ያገኙትን ከብታቸውን ሁሉ ይዘው ያዕቆብ ዘሩ ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብፅ መጡ

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 46:6
10 Referencias Cruzadas  

አብራምንም አለው፦ “ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንደሚሆኑ በእርግጥ እወቅ፥ ባርያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


ወንዶች ልጆቹንና የልጆቹን ወንዶች ልጆች፥ ሴቶች ልጆቹንና የወንዶች ልጆቹን ሴቶች ልጆች፥ ዘሩንም ሁሉ ከእርሱ ጋር ወደ ግብጽ ወሰደ።


እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፥ አሦርም ያለ ምክንያት በደለው።


አባቶቻችን ወደ ግብጽ ወረዱ፥ በግብጽም እጅግ ዘመን ተቀመጥን ግብፃውያንም እኛንና አባቶቻችንን በደሉ፤


ያዕቆብም ወደ ግብጽ ወረደ፤ እርሱም ሞተ፤ አባቶቻችንም፤


አባቶችህ ሰባ ሰው ሆነው ወደ ግብጽ ወረዱ፤ አሁን ግን ጌታ አምላክህ ብዛትህን እንደ ሰማይ ከዋክብት አደረገ።”


አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።


ለይስሐቅም ያዕቆብንና ዔሳውን ሰጠሁት፤ ለዔሳውም የሴይርን ተራራ ርስት አድርጌ ሰጠሁት፤ ያዕቆብም ልጆቹም ወደ ግብጽ ወረዱ።


ያዕቆብ ወደ ግብጽ ከገባ በኋላ፥ አባቶቻችሁ ጌታ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ ጌታም የቀድሞ አባቶቻችሁን ከግብጽ ምድር አውጥተው በዚህ ስፍራ እንዲኖሩ ያደረጉትን ሙሴንና አሮንን ላከላቸው።