La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 45:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ዮሴፍም በእርሱ ዘንድ ቆመው ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊት ሊታገሥ አልተቻለውም፦ “ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፥ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ ማንም ከአጠገቡ የቆመ አልነበረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያ ጊዜ ዮሴፍ አጠገቡ በነበሩ ሰዎች ፊት ስሜቱን ሊገታ ባለመቻሉ፣ “እዚህ ያሉትን ሰዎች በሙሉ አስወጡልኝ” ብሎ ጮኾ ተናገረ፤ ስለዚህም ዮሴፍ ራሱን ለወንድሞቹ በገለጠበት ጊዜ፣ ከርሱ ጋራ ሌላ ማንም ሰው አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ዮሴፍ የናፍቆት ስሜቱን በአገልጋዮቹ ፊት መቈጣጠር ባለመቻሉ “ሁላችሁም ከዚህ ውጡ” ብሎ አዘዘ፤ ስለዚህ ዮሴፍ ማንነቱን ለወንድሞቹ በገለጠ ጊዜ ማንም የውጪ ሰው በአጠገቡ አልነበረም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ዮሴ​ፍም በፊቱ ሰዎች ሁሉ ቆመው ሳሉ ሊታ​ገሥ አል​ተ​ቻ​ለ​ውም፥ “ሰዎ​ቹ​ንም ሁሉ ከፊቴ አስ​ወ​ጡ​ልኝ” ብሎ ተና​ገረ፤ ዮሴፍ ለወ​ን​ድ​ሞቹ ራሱን በገ​ለጠ ጊዜ በእ​ርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ዮሴፍም በእርሱ ዘንድ ቆመው ባሉት ሰዎች ሁሉ ፊት ሊታገሥ አልተቻለውም፦ ሰዎቹንም ሁሉ ከፊቴ አስወጡልኝ ብሎ ጮኽ ተናገረ ዮሴፍ ለወንድሞቹ ራሱን በገለጠ ጊዜ በእርሱ ዘንድ የቆመ ማንም አልነበረም።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 45:1
12 Referencias Cruzadas  

ከፊታቸውም ዘወር ብሎ አለቀሰ፤ ከዚያም ወደ እነርሱ ተመልሶ እንደገና አነጋገራቸው፤ ስምዖንንም ከእነርሱ ለይቶ ዐይናቸው እያየ አሰረው።


ልጁን ሳልይዝ እንዴት ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳለሁ? ፈጽሞ አላደርገውም፤ እባክህ በአባቴ ላይ የሚደርሰውን መከራ እንዳይ አታድርገኝ።”


የፍልስጥኤም ቆነጃጅት ደስ እንዳይላቸው፤ ያልተገረዙት ሴት ልጆች እልል እንዳይሉ፤ ይህን በጌት አትናገሩ፤ በአስቀሎናም መንገዶች አታውጁ፤


ከዚያም መጋገሪያውን አውጥታ እንጀራውን አቀረበችለት፤ እርሱ ግን መብላት አልፈለገም። አምኖንም፥ “ሰውን ሁሉ ከዚህ አስወጡልኝ” አለ፤ ሰውም ሁሉ ትቶት ወጣ።


ከድሮ ዘመን ጀምሮ ዝም ብያለሁ፥ ዝም ብዬም ታግሻለሁ፤ አሁን ምጥ እንደ ያዛት ሴት እጮኻለሁ፤ አጠፋለሁ በአንድነትም እጨርሳለሁ።


እኔም፦ “የጌታን ስም አላነሣም፥ ከእንግዲህ ወዲህም በስሙ አልናገርም” ብል፥ በአጥንቶቼ ውስጥ እንደ ገባ እንደሚነድድ እሳት ያለ በልቤ ሆነብኝ፤ ደከምሁ፥ መሸከምም አልቻልሁም።


በዳዊት ቤት ላይ፥ በኢየሩሳሌምም በሚኖሩት ላይ፥ የምሕረትንና የልመናን መንፈስ አፈስሳለሁ። እነርሱም ወደ እርሱ በሚመለከቱበት ጊዜ የወጉትን ይመለከታሉ። ሰውም ለአንድ ልጁ እንደሚያለቅስ ያለቅሱለታል፥ ሰውም ለበኩር ልጁ እንደሚያዝን በመራራ ኅዘን ያዝኑለታል።


“ወንድምህ ቢበድልህ፥ ሄደህ አንተና እርሱ ብቻችሁን ሆናችሁ ገሥጸው። ቢሰማህ፥ ወንድምህን ታተርፈዋለህ፤


ይኸውም ለሕዝብ ሁሉ አይደለም፤ ነገር ግን በእግዚአብሔር አስቀድሞ የተመረጡ ምስክሮች ለሆንን ለእኛ ነው እንጂ፤ ከሙታንም ከተነሣ በኋላ ከእርሱ ጋር የበላን የጠጣንም እኛ ነን።


በሁለተኛውም ዮሴፍ ለወንድሞቹ ታወቀ፤ የዮሴፍም ትውልድ በፈርዖን ዘንድ ተገለጠ።


ተገቢ ያልሆነ ነገር አያደርግም፤ ራስ ወዳድ አይደለም፤ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም።