ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም፥ እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።”
ዘፍጥረት 42:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሱም ወንድሞቹን፥ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፥ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እርሱም ወንድሞቹን፣ “ኧረ ብሬ ተመልሶልኛል፤ ይኸው ስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት” አላቸው። ሁሉም ልባቸው በድንጋጤ ተሞልቶ እየተንቀጠቀጡ በመተያየት፣ “እግዚአብሔር ምን ሊያመጣብን ይሆን?” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርሱም ለወንድሞቹ “ገንዘቤ ተመልሶልኛል፤ ይኸው በስልቻዬ ውስጥ አገኘሁት!” ብሎ ነገራቸው። ሁሉም በፍርሃት ተንቀጥቅጠው “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ነገር ምንድን ነው?” ተባባሉ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለወንድሞቹም፥ “ብሬ ተመለሰችልኝ፤ እርስዋም በዓይበቴ አፍ እነኋት” አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ፤ እየታወኩም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፥ “እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድን ነው?” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለወንድሞቹም፦ ብሬ ተመለሰችልኝ እርስዋም በዓይበቱ አፍ እነኍት አላቸው። ልባቸውም ደነገጠ እየተንቀጠቀጡም እርስ በርሳቸው ተባባሉ፦ እግዚአብሔር ያደረገብን ይህ ምንድር ነው? |
ይስሐቅም እጅግ ደነገጠ እንዲህም አለ፦ “ያደነውን አደን ወደ እኔ ያመጣ ማን ነው? አንተ ሳትመጣም ከሁሉ በላሁ ባረክሁትም፥ እርሱም የተባረከ ሆኖ ይኖራል።”
አባታቸው ያዕቆብም፥ “ያለ ልጅ እኮ አስቀራችሁኝ፤ ዮሴፍ የለም፤ ስምዖንም የለም፤ አሁን ደግሞ ብንያምን ልትወስዱ ትፈልጋላችሁ፤ ኧረ ምን ጉድ ነው የመጣብኝ!” አላቸው።
የቤቱ አዛዥም፥ “አይዞአችሁ አትፍሩ፤ በየስልቾቻችሁ ውስጥ ያገኛችሁትን ገንዘብ የሰጣችሁ የእናንተም የአባቶቻችሁም አምላክ ነው፤ እኔ እንደሆንኩ ብሩን ተቀብያለሁ” አላቸው።
በሰሎሞን ገበታ ላይ የሚቀርበውን የምግብ ዓይነት፥ የመኳንንቱን መኖሪያ አካባቢዎች፥ የቤተ መንግሥቱን ሠራተኞች የሥራ አደረጃጀት፥ የደንብ ልብሳቸውንም ዓይነት፥ በግብዣ ጊዜ የሚያገለግሉትን አሳላፊዎችና በቤተ መቅደስም የሚያቀርባቸውን መሥዋዕቶችን ሁሉ ተመለከተች፤ በዚህም ሁሉ የተሰማት አድናቆት ከጠበቀችው በላይ ነበር።
ለውዴ ከፈትሁለት፥ ውዴ ግን ፈቀቅ ብሎ አልፎ ነበር። ነፍሴ ከመራቁ የተነሣ ደነገጠች፥ ፈለግሁት፥ አላገኘሁትም፥ ጠራሁት፥ ነገር ግን አልመለሰልኝም።
ፌ። እግዚአብሔር ያሰበውን አደረገ፥ በቀድሞ ዘመን ያዘዘውን ቃል ፈጸመ፥ አፈረሰ አልራራምም፥ ጠላትንም ደስ አሰኘብሽ፥ የሚያስጨንቁሽንም ቀንድ ከፍ ከፍ አደረገ።
በጠላቶቻቸውም ምድሮች ሳሉ ከእናንተ መካከል በተረፉት ላይ በልባቸው ድንጋጤን እልክባቸዋለሁ፤ በነፋስም የምትንቀሳቀስ የቅጠል ድምፅ ታስደነብራቸዋለች፤ እነርሱም ከሰይፍ እንደሚሸሹ ይሸሻሉ፤ ማንም ሳያሳድዳቸው ይወድቃሉ።
በእነዚያ ሕዝቦች መካከል ዕረፍት አታገኝም፤ ለእግርህም ጫማ ማረፊያ ቦታ አይኖርም። በዚያም ጌታ የሚርድ ልብ፥ ፈዛዛ ዐይኖች፥ ደካማም ነፍስ ይሰጥሃል።