እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።
ዘፍጥረት 4:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ቃየንም ሚስቱን አወቀ፥ ፀነሰችም፥ ሔኖክንም ወለደች፤ ከተማም መሠረተ፤ ከተማይቱንም በልጁም ስም “ሔኖክ” ብሎ ጠራት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቃየን ሚስቱን ተገናኛት፤ እርሷም ፀንሳ ሔኖክን ወለደች። ቃየን የቈረቈረውን ከተማ በልጁ ስም ሔኖክ ብሎ ጠራው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ቃየል ሚስቱን ከተገናኘ በኋላ ፀነሰች ሔኖክንም ወለደች፤ ቃየል ከተማን መሠረተ፤ በልጁም ስም “ሔኖክ” ብሎ ጠራት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቃየልም ሚስቱን ዐወቃት፤ ፀነስችም፤ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፤ የከተማይቱንም ስም በልጁ ስም “ሄኖሕ” አላት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቃየንም ሚስቱን አወቀ ፀነሰችም፤ ሄኖሕንም ወለደች። ከተማም ሠራ፤ የከተማይቱንም ስም በልጅ ስም ሄኖሕ አላት። |
እንዲህም፦ “ኑ ለእኛ ከተማ እንመስርት፥ በዚያም ጫፉ እስከ ሰማይ የሚደርስ ግንብ እንሥራ፤ በምድር ላይ ሳንበታተንም ስማችንን እናስጠራ” አሉ።
አቤሴሎም፥ “ለስሜ መታሰቢያ የሚሆን ልጅ የለኝም” በማለት መታሰቢያ እንዲሆነው በሕይወት እያለ የንጉሥ ሸለቆ በተባለው ስፍራ ለራሱ ሐውልት አቁሞ ስለ ነበር፥ እስከ ዛሬ ድረስ የአቤሴሎም ሐውልት ተብሎ ይጠራል።