ዘፍጥረት 39:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጌታውም “ባርያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ፥ ተቈጣ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጌታውም፣ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ ሚስቱ የነገረችውን ታሪክ ሲሰማ ተቈጣ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሚስቱ “የአንተ አገልጋይ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን ታሪክ በሰማ ጊዜ የዮሴፍ አሳዳሪ እጅግ ተቈጣ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጌታውም፥ “ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ” ብላ የነገረችውን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቈጣ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጌታውም፦ ባሪያህ እንዲህ አደረገኝ ብላ የነገረችውምን የሚስቱን ቃል በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ። |
እኔም ‘ተከሳሹ በከሳሾቹ ፊት ለፊት ሳይቆም ለተከሰሰበትም መልስ ይሰጥ ዘንድ ፈንታ ሳያገኝ፥ ማንንም ቢሆን አሳልፎ መስጠት የሮማውያን ሥርዓት አይደለም፤’ ብዬ መለስሁላቸው።