La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 39:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድ ቀን ዮሴፍ የዕለት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቤት ገባ፤ ከቤቱ አገልጋዮችም አንድም ሰው በቤት ውስጥ አልነበረም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ ቀን ዮሴፍ የዕለት ተግባሩን ለማከናወን ወደ ቤት ገባ፤ ከቤቱ አገልጋዮችም አንድም ሰው በቤት ውስጥ አልነበረም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ከዕለታት አንድ ቀን ዮሴፍ ለሥራ ጉዳይ ወደ ቤት ሲገባ በቤት ውስጥ አንድም ሠራተኛ አልነበረም።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በአ​ን​ዲ​ትም ቀን እን​ዲህ ሆነ፤ በዚያ ቀን ሥራ​ውን እን​ዲ​ሠራ ዮሴፍ ወደ ቤቱ ገባ፤ በቤ​ትም ውስጥ ከቤተ ሰዎች ማንም አል​ነ​በ​ረም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እንዲህም ሆነ በዚያን ጊዜ ሥራውን እንዲሠራ ወደ ቤቱ ገባ በቤትም ውስጥ ከቤት ሰዎች ማንም አልነበረም።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 39:11
8 Referencias Cruzadas  

ምንም እንኳ ዮሴፍን በየቀኑ ብትጐተጉተውም፥ አልሰማትም፤ ከእርሷ ጋር መተኛቱ ይቅርና አብሯትም መሆን አልፈቀደም።


እርሷም ልብሱን ጨምድዳ ይዛ “በል አብረኸኝ ተኛ” አለችው። እርሱ ግን ልብሱን እጇ ላይ ጥሎ ሸሽቶ ከቤት ወጣ።


የአመንዝራ ሰው ዐይን ጨለማን ይጠብቃል፦ የማንም ዐይን አያየኝም ይላል፥ ፊቱንም ይሸፍናል።


“የስርቆት ውኃ ይጣፍጣል፥ የተሸሸገም እንጀራ ደስ ያሰኛል።”


ሰው በስውር ቦታ ቢሸሸግ፥ እኔ አላየውምን? ይላል ጌታ። ሰማይንና ምድርንስ የሞላሁ እኔ አይደለሁምን? ይላል ጌታ።


ለፍርድ ወደ እናንተ እቀርባለሁ፤ በአስማተኞች፥ በዘማውያን፥ በሐሰት በሚምሉ፥ የሠራተኛውን ደመወዝ በሚያስቀሩ፥ መበለቲቱንና የሙት ልጅን በሚያስጨንቁ፥ ስደተኛውን በሚገፉ፥ እኔንም በማይፈሩ ላይ ፈጣን ምስክር እሆንባቸዋለሁ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ያስነውራል።


ለቅዱሳን የማይገባው፥ ማንኛውም የዝሙትና የርኩሰት፥ ወይም የስስት ነገር ሁሉ በእናንተ ዘንድ ከቶ አይሰማ፤