ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስለዚህ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ልጆቹን በወለደች ጊዜ ይስሐቅ ሥልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።
ዘፍጥረት 38:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፥ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በምትወልድበትም ጊዜ አንደኛው እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም፣ “ይህኛው መጀመሪያ ወጣ” ስትል በእጁ ላይ ቀይ ክር አሰረችለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በምትወልድበትም ጊዜ ከመንትያዎቹ አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ሴት ቀይ ክር በእጁ ላይ አሰረችለትና “ይህ በመጀመሪያ ወጣ” አለች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስትወልድም አንዱ እጁን አወጣ፤ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አሰረች፥ “ይህ መጀመሪያ ይወጣል” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስትውልድም አንድ እጁን አወጣ አዋላጂቱም ቀይ ፈትል ወስዳ በእጁ አስረች፦ ይህ መጀመሪያ ይወጣል አለች። |
ከዚያም በኋላ ወንድሙ ወጣ፥ በእጁም የዔሳውን ተረከዝ ይዞ ነበር፤ ስለዚህ ስሙ ያዕቆብ ተባለ። ልጆቹን በወለደች ጊዜ ይስሐቅ ሥልሳ ዓመት ሆኖት ነበር።