La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 38:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ይሁዳም፥ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፤ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

ይሁዳም፣ “እንግዲህ መያዣውን እንደ ያዘች ትቅር፣ አለዚያ መሣቂያ እንሆናለን። ለነገሩማ ይህን ፍየል ላክሁ፤ አንተም ፈልገህ አላገኘሃትም” አለ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ይሁዳም “እንግዲህ ጠቦቱን ልኬላት ነበር፤ ነገር ግን ልታገኛት አልቻልክም፤ ስለዚህ ሰዎች መሳቂያ እንዳያደርጉን የወሰደችውን መያዣ እዚያው ታስቀረው” አለ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ይሁ​ዳም፥ “እኛ መዘ​በቻ እን​ዳ​ን​ሆን ትው​ሰ​ደው፤ እነሆ፥ የፍ​የ​ሉን ጠቦት ላክ​ሁ​ላት፤ አን​ተም አላ​ገ​ኘ​ሃ​ትም” አለ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ይሁዳም፦ እኛ መዘበቻ እንዳንሆን ትውሰደው እነሆ የፍየሉን ጠቦት ሰደድሁላት አንተም አላገኘሃትም አለ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 38:23
8 Referencias Cruzadas  

መልእክተኛውም ወደ ይሁዳ ተመልሶ፥ “ሴቲቱን ላገኛት አልቻልኩም፤ ነዋሪዎቹም ‘በዚህ አካባቢ እንደዚህች ያለች ዝሙት ዐዳሪ የለችም’ አሉኝ” ብሎ ነገረው።


ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።


ታዲያ በፊቱ ክፉ ነገር በማድረግ፥ የጌታን ቃል ያቃለልኸው ስለምንድን ነው? ሒታዊውን ኦርዮን በሰይፍ መታህ፤ ሚስት እንድትሆንህም ሚስቱን ወሰድሃት፤ እርሱንም በአሞናውያን ሰይፍ ገደልኸው።


ቁስልንና ውርደትን ያገኛል፥ ስድቡም አይደመሰስም።


ታዲያ አሁን ከምታፍሩበት ነገር ሌላ ያንጊዜ ምን ፍሬ ነበራችሁ? የእነዚህ ነገሮች መጨረሻ ሞት ነውና።


የሚያሳፍረውን ስውር ነገር ጥለናል፤ በተንኮል አንመላለስም ወይም የእግዚአብሔርን ቃል በውሸት አንቀላቅልም፤ እውነትን በመግለጥ ግን በእግዚአብሔር ፊት ለሰው ሕሊና ሁሉ ራሳችንን እናቀርባለን።


እነርሱ በስውር ስለሚያደርጉት መናገር እንኳን ያስነውራል።


“እነሆ እንደ ሌባ እመጣለሁ፤ ራቁቱን እንዳይሄድ ኀፍረቱንም እንዳያዩ ነቅቶ ልብሱን የሚጠብቅ ብፁዕ ነው።”