የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።
ዘፍጥረት 38:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፥ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፣ ሻሿን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚያ በኋላ ሻሽዋን ከፊቷ ላይ አንሥታ የመበለትነት ልብሷን እንደገና ለበሰች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም ተነሥታ ሄደች፤ መጐናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነቷን ልብስ ለበሰች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤስውም ተነሥታ ሄደች መጎናጸፊያዋንም አውልቃ የመበለትነትዋን ልብስ ለበስች። |
የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።
“ታዲያ ምን መያዣ ልስጥሽ?” አላት። እርሷም፥ “የማኅተም ቀለበትህን ከነማሰሪያው፥ እንደዚሁም ይህን በትርህን ስጠኝ” አለችው። የጠየቀችውን ሁሉ ሰጣትና አብሯት ተኛ፤ እርሷም ፀነሰች።
ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፥ መልእክተኛው ግን ሴትዮዋን ሊያገኛት አልቻለም።
ስለዚህም ኢዮአብ ወደ ተቆዓ ሰው ልኮ አንዲት ብልኅ የሆነች ሴት አስመጣ፤ እንዲህም አላት፤ “ኀዘንተኛ በመምሰል የኀዘን ልብስ ልበሺ፤ ዘይት አትቀቢ፤ ለሞተ ሰው ብዙ ጊዜ እንዳዘነች ሴት ትሆኛለሽ፤