La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 38:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፥ ኤራስ ወደ ተባለ ዓዶሎማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ፣ ኤራ ወደ ተባለ ዓዶላማዊ ሰው ወረደ፤ እርሱም ዘንድ ለመኖር ቤቱ ገባ።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዚያም ወራት ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ሒራ ወደሚሉት ዐዱላማዊ ሰው ዘንድ ሄዶ መኖሪያውን እዚያ አደረገ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዚ​ያም ወራት እን​ዲህ ሆነ፤ ይሁዳ ከወ​ን​ድ​ሞቹ ተለ​ይቶ ወረደ፤ ስሙ ኤራስ በሚ​ባል በዓ​ዶ​ሎ​ማ​ዊ​ውም ሰው ዘንድ አደረ።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዚያም ወራት እንዲህ ሆነ ይሁዳ ከወንድሞቹ ተለይቶ ወረድ፥ ስሙን ኤራስ ወደሚሉት ወደ ዓዶሎማዊውም ሰው ገባ።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 38:1
12 Referencias Cruzadas  

ከብዙ ጊዜ በኋላ የሹዓ ልጅ፥ የይሁዳ ሚስት ሞተች። ይሁዳ ከሐዘኑ ከተጽናና በኋላ ከዓዶላማዊው ከሒራ ጋር የበጎቹን ጠጉር የሚሸልቱ ሰዎች ወዳሉበት ወደ ተምና ሄደ።


ይሁዳ በመያዣ ስም የሰጣትን ዕቃዎች ለማስመለስ የፍየሉን ጠቦት በዓዶሎማዊ ወዳጁ እጅ ላከላት፥ መልእክተኛው ግን ሴትዮዋን ሊያገኛት አልቻለም።


ከሠላሳውም አለቆች ሦስቱ ወርደው በመከር ጊዜ ወደ ዳዊት ወደ ዓዱላም ዋሻ መጡ፥ የፍልስጥኤማውያንም ጭፍራ በራፋይም ሸለቆ ሰፍሮ ነበር።


አንድ ቀን ኤልሳዕ አንዲት ሀብታም ሴት ወደምትኖርበት ወደ ሱነም ሄደ፤ እርሷም ምግብ እንዲበላ ጋበዘችው፤ ከዚያን ዕለት ጀምሮ ወደ ሱነም በሚመጣበት ጊዜ ሁሉ በቤትዋ ይመገብ ነበር፤


ከጠቢባን ጋር የሚሄድ ጠቢብ ይሆናል፥ የሰነፎች ባልንጀራ ግን ክፉ መከራን ይቀበላል።


አላዋቂነትን ትታችሁ በሕይወት ኑሩ፥ በማስተዋልም መንገድ ሂዱ።”


በማሬሻ የምትቀመጪ ሆይ፥ ወራሽ አመጣብሻለሁ፤ የእስራኤል ክብር ወደ ዓዱላም ይመጣል።


የልብና ንጉሥ፥ የዓዶላም ንጉሥ፥


የርሙት፥ ዓዶላም፥ ሰኰት፥ ዓዜቃ፥


ያዔልም ወጥታ ሲሣራን ተቀበ ለችውና፥ “ጌታዬ፤ ወደ ውስጥ ግባ፤ ፈጽሞ አትፍራ” አለችው፤ ሲሣራም ወደ ድንኳኗ ገባ፤ እርሷም በልብስ ሸፍና ደበቀችው።


ዳዊት ከጋት ተነስቶ ወደ ዓዶላም ዋሻ ሸሸ፤ ወንድሞቹና የአባቱ ቤተሰቦች ይህን በሰሙ ጊዜ፥ እርሱ ወዳለበት ወደዚያው ወረዱ።