ዘፍጥረት 37:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ፥ የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም የዮሴፍን እጀ ጠባብ ወሰዱ፤ አንድ ፍየልም ዐርደው እጀ ጠባቡን በደሙ ነከሩት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አንድ ፍየል ዐረዱና የዮሴፍን ልብስ በደም ነከሩት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ፤ የፍየልም ጠቦት አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የዮሴፍንም ቀሚስ ወሰዱ የፍየል አውራም አርደው ቀሚሱን በደም ነከሩት። |
እንዲህም ብለው ነገሩት፦ “ዮሴፍ ገና በሕይወቱ አለ፥ እርሱም በግብጽ ምድር ላይ ሁሉ ገዥ ሆኖአል።” ያዕቆብም ልቡ ደነገጠ፥ ሊያምናቸውም አልቻለም።