ዘፍጥረት 30:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ “እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ” አለች፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ፀንሳ፣ ወንድ ልጅ ወለደችና “እግዚአብሔር ዕፍረቴን አስወገደልኝ” አለች፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ፀንሳም ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር ወንድ ልጅ ሰጠኝ፤ ስድቤንም አስወገደልኝ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወንድ ልጅንም ለያዕቆብ ወለደችና፥ “እግዚአብሔር ሽሙጤን ከእኔ አስወገደ” አለች፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ፀነሰችም፥ ወንድ ልጅንም ወለደችና፦ እግዚአብሔር ስድቤን አስወገደ አለች፤ |
በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።
ነገር ግን አንድ ነገር ብቻ እንድትፈቅድልኝ እለምንሃለሁ፤ ከእንግዲህ ባል ስለማላገባ ከባልንጀሮቼ ጋር ወደ ተራሮች ወጥቼ እየዞርሁ ሁለት ወር እንዳለቅስ አሰናብተኝ።”