ዘፍጥረት 30:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም፦ “ባርያዬን ለባሌ ስለ ሰጠሁ እግዚአብሔር ዋጋዬን ሰጠኝ” አለች፥ ስሙንም ይሳኮር ብላ ጠራችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያም፣ “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ክሶኛል” አለች፤ ስሙንም ይሳኮር ብላ አወጣችለት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያም “አገልጋዬን ለባሌ በመስጠቴ እግዚአብሔር ደመወዜን ከፈለኝ” ስትል ይሳኮር ብላ ጠራችው፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም፥ “የልጄን እንኮይ ስለ ሰጠሁ እግዚአብሔር ዋጋዬን ሰጠኝ” አለች፤ ስሙንም ይሳኮር ብላ ጠራችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም ባሪያዬን ለባሌ ስለ ሰጠሁ እግዚአብሔር ዋጋዬን ሰጠኝ አለች፤ ስሙንም ይሳኮር ብላ ጠራችው። |
እስራኤልም የሚገባውን እንዲፈጽም የዘመኑን ሁኔታ የሚያውቁ ጥበበኞች ሰዎች የይሳኮር ልጆች አለቆች ሁለት መቶ ነበሩ፤ ወንድሞቻቸውም ሁሉ ይታዘዙአቸው ነበር።