La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 3:1 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ጌታ እግዚአብሔርም ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ እባብ ተንኰለኛ ነበረ። ሴቲቱንም፦ “በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ አንዳች እንዳትበሉ አዝዞአልን?” አላት።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እባብ እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው የዱር አራዊት ሁሉ ተንኰለኛ ነበረ፤ ሴቲቱንም፣ “በርግጥ እግዚአብሔር፣ ‘በአትክልቱ ስፍራ ካሉ ዛፎች ከማናቸውም እንዳትበሉ’ ብሏልን?” አላት።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠራቸው አራዊት ሁሉ፥ እባብ እጅግ ተንኰለኛ ነበረ፤ ስለዚህ እባብ “በአትክልቱ ቦታ ካሉት ዛፎች ሁሉ ፍሬ እንዳትበሉ በእርግጥ እግዚአብሔር አዞአችኋልን?” ሲል ሴቲቱን ጠየቃት።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

እባ​ብም እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አም​ላክ ከፈ​ጠ​ራ​ቸው ከም​ድር አራ​ዊት ሁሉ ይልቅ ተን​ኰ​ለኛ ነበር። እባ​ብም ሴቲ​ቱን “እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በገ​ነት ካለው ዛፍ ሁሉ አት​ብሉ ያላ​ችሁ ለም​ን​ድን ነው?” አላት።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

እባብም እግዚአብሔር አምላክ ከፈጠረው ከምድር አውሬ ሁሉ ይልቅ ተንኵለኚ ነበረ። ሴቲቱንም፤ በውኑ እግዚአብሔር ከገነት ዛፍ ሁሉ እንዳትበሉ አዝዞአል? አላት።

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 3:1
14 Referencias Cruzadas  

ቢወድቁ አንዱ ሁለተኛውን ያነሣዋልና፥ አንዱ ብቻውን ሆኖ በወደቀ ጊዜ ግን የሚያነሣው ሁለተኛ የለውምና ወዮለት።


በዚያም ቀን ጌታ ፈጣኑን እባብ ሌዋታንን፥ የሚጠቀለለውንም እባብ ሌዋታንን፥ በጠንካራ በታላቅ፥ በብርቱም ሰይፍ ይቀጣል፤ በባሕርም ውስጥ ያለውን ዘንዶ ይገድላል።


“እነሆ እንደ በጎች በተኩላዎች መካከል እልካችኋለሁ፤ ስለዚህ እንደ እባብ ብልሆች እንደ ርግብም የዋሆች ሁኑ።


ፈታኙ መጥቶ “የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ እነዚህ ድንጋዮች እንጀራ እንዲሆኑ እዘዝ” አለው።


“‘መላእክቱን ስለ አንተ ያዝልሃል፤ እግርህም በድንጋይ ከቶ እንዳትሰናከል በእጃቸው ያነሡሃል’ ተብሎ ተጽፎአልና የእግዚአብሔር ልጅ ከሆንህ፥ ራስህን ወደ ታች ወርውር” አለው።


“ወድቀህ ብትሰግድልኝ ይህን ሁሉ እሰጥሃለሁ” አለው።


ይህም አያስገርምም! ሰይጣን ራሱ የብርሃንን መልአክ መስሎ ራሱን ለውጦ ይቀርባል።


ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ሊኖራችሁ ከሚገባ ቅንነትና ንጽሕና እንዳትርቁ ብዬ እፈራለሁ።


እናንተም ባሎች ሆይ! ጸሎታችሁ እንዳይደናቀፍ ከሚስቶቻችሁ ጋር በመተሳሰብ ኑሩ፤ የሕይወትንም ጸጋ አብረዋችሁ ስለሚወርሱ እንደ ደካማነታቸው ሴቶችን አክብሯቸው።


እባቡም ሴቲቱ በወንዝ እንድትወሰድ ወንዝ የሚያህልን ውሃ ከአፉ በስተኋላዋ አፈሰሰ።


ታላቁም ዘንዶ ወደ ታች ተጣለ፤ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው፥ ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀደመው እባብ ተጣለ፤ ወደ ምድር ተጣለ፤ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ።


ዲያብሎስና ሰይጣን የተባለውን፥ የቀደሞውን እባብ፥ ዘንዶውን ያዘው፤