መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፥ ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጉድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር።
ዘፍጥረት 29:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱም አሉ፦ “መንጎች ሁሉ እስኪከማቹና ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም፥ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነርሱም፣ “መንጎቹ ሁሉ ተሰብስበው ድንጋዩ ከጕድጓዱ አፍ ካልተንከባለለ በቀር አንችልም፤ ከዚያም በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱም “እረኞች ሁሉ መንጋዎቻቸውን ይዘው እዚህ ከመሰብሰባቸው በፊት ምንም ማድረግ አንችልም፤ ሁሉም እዚህ ከመጡ በኋላ ግን ድንጋዩን በኅብረት አንከባለን በጎቹን እናጠጣቸዋለን” አሉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነርሱም አሉ፥ “እረኞች ሁሉ ካልተሰበሰቡና ድንጋዪቱን ከጕድጓዱ አፍ ካላነሡአት በቀር አንችልም፤ ከዚያም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነርሱም አሉ፦ መንጎች ሁሉ እስኪገለብጡት ድረስ አንችልም ከዚይም በኋላ በጎቹን እናጠጣለን። |
መንጎችም ሁሉ ከዚያ በተከማቹ ጊዜ ድንጋዩን ከጉድጓዱ አፍ ገለል አድርገው በጎቹን ያጠጡ ነበር፥ ድንጋዩንም ወደ ስፍራው መልሰው በጉድጓዱ አፍ እንደገና ይገጥሙት ነበር።
ለዮሴፍ ለብቻው ቀረበለት፤ ለወንድሞቹም ለብቻቸው ቀረበላቸው፤ እንዲሁም ከእርሱ ጋር ለሚበሉት ግብፃውያን ደግሞ ሌላ ገበታ ቀረበላቸው፤ ምክንያቱም ግብፃውያን ከዕብራውያን ጋር አብሮ መመገብን እንደ ጸያፍ ይቈጥሩት ነበር።
በከተማዪቱ መዳረሻ ያለውን ኰረብታ በመውጣት ላይ ሳሉ፥ ውሃ ለመቅዳት የሚወጡ ልጃገረዶችን አግኝተው፥ “ባለ ራእዩ እዚህ አለን?” ሲሉ ጠየቋቸው።