ዘፍጥረት 29:35 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ደግሞም ፀነስች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፥ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንደ ገና ፀንሳ አሁንም ወንድ ልጅ ወለደች፤ እርሷም፣ “እንግዲህ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስሙንም ይሁዳ ብላ ጠራችው። ከዚያም በኋላ መውለድ አቆመች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንደገና ፀነሰችና ወንድ ልጅ ወለደች፤ “አሁንስ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” ስትል ስሙን ይሁዳ አለችው፤ ከዚህ በኋላ መውለድ አቋረጠች። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ደግሞም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፤ በዚህም ጊዜ “እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ” አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ደግሞም ፀነስች ወንድ ልጅንም ወለደች በዚህም ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ አለች፤ ስለዚህም ስሙን ይሁዳ ብላ ጠራችው። መውለድንም አቆመች። |
“የይሁዳ ልጆች በየትውልዳቸው፥ በየወገኖቻቸው፥ በየአባቶቻቸው ቤቶች፥ እንደየስማቸው ቍጥር፥ ዕድሜው ሀያ ዓመት የሆነውንና ከዚያም በላይ ያለው፥ ወደ ጦርነት የሚወጣው ሁሉ፥
ስለ ይሁዳም እንዲህም አለ፦ “ጌታ ሆይ፥ የይሁዳን ድምፅ ስማ፥ ወደ ወገኖቹም አምጣው። እጆቹንም አጠንክርለት፤ ከጠላቶቹ ጋር ሲዋጋም ረዳት ሁነው።”