የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
ዘፍጥረት 29:32 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ልያም ፀነሰች፥ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልያ ፀነሰች፤ ወንድ ልጅም ወለደች፤ “እግዚአብሔር መከራዬን ስለ ተመለከተልኝ፣ ከእንግዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል አለችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልያ ፀንሳ ወንድ ልጅ ወለደች፤ “እግዚአብሔር መከራዬን ተመለከተ፤ ከእንግዲህስ ወዲያ ባሌ ይወደኛል” ስትል ስሙን ሮቤል አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ልያም ፀነሰች፤ ወንድ ልጅንም ወለደች፥ ስሙንም ሮቤል ብላ ጠራችው፥ “እግዚአብሔር መዋረዴን አይቶአልና፥ እንግዲህስ ወዲህ ባሌ ይወድደኛል” ስትል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ልያም ፀነሰች ወንድ ልጅንም ወለደች ስሙም ሮቤል ብላ ጠራችው እግዚአብሔር መከራዬን አይቶአልና፥ እንግዲህም ወዲህ ባሌ ይወድደኛል ብላለችና። |
የእግዚአብሔር መልአክም አላት፦ እነሆ አንቺ ፀንሰሻል፥ ወንድ ልጅንም ትወልጃለሽ፥ ስሙንም እስማኤል ብለሽ ትጠሪዋለሽ፥ እግዚአብሔር መቸገርሽን ሰምቶአልና።
የአባቴ አምላክ፥ የአብርሃም አምላክ የይስሐቅም ፍርሃት፥ ከእኔ ጋር ባይሆን ኖሮ፥ ዛሬ ባዶ እጄን በሰደድኸኝ ነበር፥ እግዚአብሔር መከራዬንና የእጆቼን ልፋት አየ፥ ትናንትና ሌሊትም ገሠጸህ።”
እስራኤልም በዚያች አገር በተቀመጠ ጊዜ ሮቤል ሄደ የአባቱንም ቁባት ባላን ተገናኛት፥ እስራኤልም ሰማ። የያዕቆብም ልጆች ዐሥራ ሁለት ናቸው፥
ሮቤልም መልሶ፥ “በዚህ ልጅ ላይ፥ ‘ክፉ ነገር አታድርጉ’ ብዬ አልነበረምን? እናንተ ግን አልሰማችሁኝም፤ ስለዚህም ደሙ ከእጃችን ይፈለጋል” አላቸው።
የእስራኤልም በኩር የሮቤል ልጆች እነዚህ ናቸው። እርሱ የበኩር ልጅ ነበረ፤ ነገር ግን የአባቱን ምንጣፍ ስላረከሰ ብኩርናው ለእስራኤል ልጅ ለዮሴፍ ልጆች ተሰጠ፤ ትውልዱ ግን ከብኩርናው ጋር አልተቈጠረም።
ጌታም አለ፦ “በግብጽ ያለውን የሕዝቤን መከራ በእውነት አየሁ፥ በአስገባሪዎቻቸውም ምክንያት የሚጮሁትን ጩኸት ሰማሁ፤ ሥቃያቸውንም አውቄአለሁ።
እንዲህም ብላ ስእለት ተሳለች፤ “የሠራዊት ጌታ ሆይ፤ የአገልጋይህን መዋረድ ተመልክተህ ብታስበኝ፥ ለአገልጋይህም ወንድ ልጅ ብትሰጣት፥ በሕይወት ዘመኑ ሁሉ ለጌታ እሰጠዋለሁ፤ ምላጭም በራሱ ላይ አያርፍም።”