ዘፍጥረት 29:28 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ያዕቆብም እንዲህ አደረገ፥ ይህችንም ሳምንት ፈጸመ፥ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ሰጠው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ያዕቆብም በነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋራ ተሞሽሮ ሰባት ቀን ከቈየ በኋላ፣ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ዳረለት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ያዕቆብም በነገሩ ተስማማ፤ ከልያ ጋር ሰባት ቀን ተሞሽሮ ከቈየ በኋላ፥ ላባ ልጁን ራሔልን ለያዕቆብ ዳረለት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ያዕቆብም እንዲህ አደረገ፤ ለዚችም ሰባት ዓመት ፈጸመ፤ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆነው ዘንድ ሰጠው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ያዕቆብም እንዲህ አደረገ ይህችንም ሳምንት ፈጸመ፤ ልጁን ራሔልንም ለእርሱ ሚስት ትሆን ዘንድ ሰጠው። |