ዘፍጥረት 29:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም ለልጁ ለልያ ባርያይቱን ዘለፋን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም ዘለፋ የተባለች አገልጋዩን ለልጁ ለልያ ደንገጥር እንድትሆን ሰጣት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባ ሴት አገልጋዩን ዚልፋን አገልጋይዋ እንድትሆን ለልጁ ለልያ ሰጣት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ለልጁ ልያ አገልጋዪቱን ዘለፋን አገልጋይ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ለልጁ ለልያ ባሪያይቱን ዘለፋን ባርያ ትሆናት ዘንድ ሰጣት። |
በነጋም ጊዜ እነሆ ልያ ሆና ተገኘች፥ ላባንም፦ “ምነው እንደዚህ አደረግህብኝ? ያገለግልሁህ ስለ ራሔል አልነበረምን? ለምን አታለልኸኝ?” አለው።