ዘፍጥረት 29:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም ያዕቆብን፦ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ደመወዝህ ምንድነው? ንገረኝ” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባ ያዕቆብን፣ “ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነጻ ልታገለግለን አይገባምና ደመወዝህ ምንድን ነው?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባ ያዕቆብን “ዘመዴ በመሆንህ ብቻ በነጻ ልታገለግለኝ አይገባህም፤ ስለዚህ ምን ያኽል ደመወዝ ላስብልህ?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ያዕቆብን፥ “ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ አታገለግለኝም ደመወዝህ ምንድን ነው? ንገረኝ” አለው መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም ያዕቆብን፦ ወንድሜ ስለሆንህ በከንቱ ታገለግለኛለህን? ምንዳህ ምንድር ነው? ንገረኝ አለው። |
እነዚህን ሃያ ዓመታት በአንተ ቤት ነበርሁ፥ ዐሥራ አራት ዓመት ስለ ሁለቱ ሴቶች ልጆችህ፥ ስድስት ዓመትም ስለ በጎችህ ተገዛሁልህ፥ ደመወዜንም ዐሥር ጊዜ ለዋወጥኸው።
የእናቱ ዘመዶች ስለ እርሱ ሆነው እነዚህን ቃሎች ሁሉ ለሴኬም ነዋሪዎች በሙሉ ነገሩ፤ “እርሱማ ወንድማችን አይደል” ብለዋልና፥ አቤሜሌክንም ለመከተል ልባቸው ወደሱ አዘነበለ።