ዘፍጥረት 29:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ላባም፦ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም ላባም ያዕቆብን፣ “አንተማ የዐጥንቴ ፍላጭ፣ የሥጋዬ ቍራጭ ነህ” አለው። ያዕቆብ አንድ ወር ሙሉ ዐብሮት ከተቀመጠ በኋላ፣ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ላባም “በእርግጥ አንተ ቅርብ የሥጋ ዘመዴ ነህ” አለው፤ ያዕቆብም አንድ ወር ያኽል ከአጐቱ ጋር ተቀመጠ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ላባም ያዕቆብን፥ “በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ፤ ከእኔ ጋር ተቀመጥ” አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ላባም፦ በእውነት አንተ አጥንቴ ሥጋዬም ነህ አለው። አንድ ወር የሚያህልም ከእርሱ ጋር ተቀመጠ። |
አዳምም አለ፥ “ይህች አጥንት ከአጥንቴ የተገኘች ናት፥ ከሥጋዬም የተገኘች ሥጋ ናት፤ ሴት ተብላ ትጠራ፥ ከወንድ የተገኘች ስለ ሆነች ‘ሴት’ ትባል” አለ።
“የሴኬምን ነዋሪዎች ሁሉ እንዲህ ብላችሁ ጠይቋቸው፤ ‘ሰባዎቹ የይሩባኣል ልጆች ቢገዟችሁ ይሻላል ወይስ አንድ ሰው ብቻ?’ የሥጋችሁ ቁራጭ፥ ያጥንታችሁ ፍላጭ መሆኔን ልብ በሉ።”