La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ዘፍጥረት 25:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፥

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይሥሐቅ አወረሰው፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አብርሃም ያለውን ሀብት ሁሉ ለይስሐቅ አወረሰው፤

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አብ​ር​ሃ​ምም በሕ​ይ​ወቱ ሳለ ገን​ዘ​ቡን ሁሉ ለልጁ ለይ​ስ​ሐቅ ሰጠው፤

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አብርሃምም የነበረውን ሁሉ ለይስሐቅ ሰጠው፤

Ver Capítulo



ዘፍጥረት 25:5
18 Referencias Cruzadas  

እግዚአብሔርም ጌታዬን እጅግ ባረከው፥ አገነነውም፥ በጎችንና ላሞችን፥ ብርንም፥ ወርቅንም፥ ወንዶች ባርያዎችንና ሴቶች ባርያዎችን፥ ግመሎችንም፥ አህዮችንም ሰጠው።


ሣራም የጌታዬ ሚስት በእርጅናው ለጌታዬ ወንድ ልጅን ወለደች፥ የነበረውንም ሁሉ ሰጠው።


የምድያምም ልጆች ዔፋ፥ ዔፈር፥ ሐኖክ፥ አቢዳዕና ኤልዳዓ ናቸው፤ እነዚህ ሁሉ የኬጡራ ልጆች ናቸው።


በግና ላም ከብትም ሎሌዎችም እጅግ በዙለት፥ የፍልስጥኤም ሰዎች ቀኑበት።


የእግዚአብሔር ሠረገላዎች የብዙ ብዙ ሺህ ናቸው፥ ጌታ በመቅደሱ በሲና በመካከላቸው ነው።


ሁሉም ነገር በአባቴ ለእኔ ተሰጥቶአል፤ ከአብ በቀር ወልድን የሚያውቅ የለም፤ ከወልድና ወልድም ሊገለጥለት ከሚፈቅደው በቀር አብን የሚያውቅ የለም።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ይህም በሥጋ ሁሉ ላይ ሥልጣን እንደ ሰጠኸው፥ ለሰጠኸው ሁሉ የዘለዓለምን ሕይወት እንዲሰጣቸው ነው።


አባት ልጁን ይወዳል፥ ሁሉንም በእጁ ሰጥቶታል።


ልጆች ከሆንን ወራሾች ደግሞ ነን፤ ከእርሱ ጋር የክብሩ ተካፋዮች እንድንሆን ከእርሱ ጋር መከራ ብንቀበል የእግዚአብሔር ወራሾችና ከክርስቶስም ጋር አብረን ወራሾች ነን።


ለገዛ ልጁ ያልራራለት ነገር ግን ስለ ሁላችን አሳልፎ የሰጠው እርሱ፥ ከእርሱ ጋር ደግሞ ሁሉን ነገር እንዲያው እንዴት አይሰጠንም?


የክርስቶስ ከሆናችሁ ስለዚህ የአብርሃም ዘር ናችሁ፥ በተስፋውም ቃል መሠረት ወራሾች ናችሁ።


ወንድሞች ሆይ! እናንተም እንደ ይስሐቅ የተስፋ ቃል ልጆች ናችሁ።


እግዚአብሔር ሙላቱ ሁሉ በእርሱ በማደሩ ተደስቷል፤


በእነዚህ በኋለኞቹ ዘመናት ግን፥ ሁሉን ወራሽ ባደረገው ደግሞም ዓለማትን በፈጠረበት በልጁ ለእኛ ተናገረን፥፥