ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦
ዘፍጥረት 23:12 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት እጅ ነሣ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃም እንደ ገና የአገሬውን ሕዝብ እጅ ነሣና አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አብርሃም ግን በሒታውያን ፊት እንደገና እጅ ነሣና፥ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም በሀገሩ ሕዝብ ሁሉ ፊት ሰገደ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብርሃምም በአገሩ ሰዎች ፊት ሰገደ፤ |
ዓይኑንም አነሣና እነሆ፥ ሦስት ሰዎች በፊቱ ቆመው አየ፥ ባያቸውም ጊዜ ሊቀበላቸው ከድንኳኑ ደጃፍ ተነሥቶ ሮጠ፥ ወደ ምድርም ሰገደ፥ እንዲህም አለ፦
ሁለቱም መላእክት በመሸ ጊዜ ወደ ሰዶም ገቡ፥ ሎጥም በሰዶም በር ተቀምጦ ነበር። ሎጥም ባያቸው ጊዜ ሊቀበላቸው ተነሣ። ፊቱንም ደፍቶ ወደ ምድር ሰገደ፥ አላቸውም፦
“አይደለም፥ ጌታዬ፥ ስማኝ፥ እርሻውን በክልሉ ውስጥ ካለው ዋሻ ጋር ሰጥቼሃለሁ፤ ሙታንህን እንድትቀብርበት በወገኖቼ በሒታውያን ፊት ሰጥቼሃለሁ።”
የአገሩ ሰዎችም እየሰሙ ለኤፍሮን እንዲህ ሲል ተናገረ፦ “ፈቃድህ ከሆነ፥ አድምጠኝ፤ የእርሻውን ዋጋ እሰጥሃለሁ፥ አንተም ከእኔ ተቀበለኝና የሚስቴን አስክሬን እዚያ ወስጄ ልቅበር” አለው።