ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
ዘፍጥረት 21:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አብርሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍን ተከለ፥ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አብርሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍ ተከለ፤ በዚያም እግዚአብሔር የዘላለም አምላክን ስም ጠራ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ አብርሃም በቤርሳቤህ የታማሪስክ ዛፍ ተከለና ለዘለዓለማዊው አምላክ ለእግዚአብሔር ሰገደ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አብርሃምም በዐዘቅተ መሐላ አጠገብ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘለዓለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አብረሃምም በቤርሳቤህ የተምር ዛፍን ተከለ፤ በዚያም የዘላለሙን አምላክ የእግዚአብሔርን ስም ጠራ። |
ከዚያም በቤቴል ምሥራቅ ወዳለው ተራራ ወጣ፥ በዚያም ቤቴልን ወደ ምዕራብ ጋይን ወደ ምሥራቅ አድርጎ ድንኳኑን ተከለ፥ በዚያም ለእግዚአብሔር መሠውያን ሠራ የእግዚአብሔርንም ስም ጠራ።
ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።
ጌታ ግን እውነተኛ አምላክ ነው፤ እርሱም ሕያው አምላክና የዘለዓለም ንጉሥ ነው፤ ከቁጣው የተነሣ ምድር ትንቀጠቀጣለች፤ አሕዛብም መዓቱን መቋቋም አይችሉም።
አሺማ በምትባል የሰማርያ ጣኦት የሚምሉና፦ ‘ዳን ሆይ! ሕያው አምላክህን!’ ደግሞ፦ ‘ሕያው የቤርሳቤህን መንገድ!’ ብለው የሚምሉ፥ እነርሱ ይወድቃሉ፥ ዳግመኛም አይነሡም።”
ጌታ አምላኬ፥ ቅዱሴ ሆይ፥ አንተ ከጥንት ጀምሮ አልነበርህምን? እኛ አንሞትም፤ ጌታ ሆይ፥ ለፍርድ ወስነሃቸዋል፥ ዓለት ሆይ ለተግሣጽም መሠረትሃቸው።