ዘፍጥረት 19:34 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፦ “እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፥ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱም ታላቂቱ ልጅ ታናሺቱን፣ “እኔ ትናንትና ማታ ከአባቴ ጋራ ተኝቻለሁ፤ ዛሬም እንደ ገና የወይን ጠጅ እናጠጣው፤ አንቺም ደግሞ ከርሱ ዘንድ ገብተሽ ተኚ፤ በዚህም የትውልድ ሐረጋችን እንዳይቋረጥ ከአባታችን ዘር ማትረፍ እንችላለን” አለቻት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ታላቂቱ ልጅ እኅቷን “ትናንት ማታ እኔ ከእርሱ ጋር ተኝቼአለሁ፤ ዛሬም እንደገና የወይን ጠጅ አጠጥተን እናስክረውና አንቺም አብረሽው ተኚ፤ በዚህ ዐይነት ሁለታችንም ከአባታችን ልጆች ወልደን ዘራችን እንዳይጠፋ እናድርግ” አለቻት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፥ “እነሆ፥ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፤ ዛሬ ሌሊት ደግሞ ወይን እናጠጣው፤ አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፤ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፤ እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ ከአባታችንም ዘር እናስቀር። |
አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።
ርኩስን ነገር ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥” ይላል ጌታ።
አስጸያፊ ነገርን ስለ ሠሩ አፍረዋልን? ምንም አላፈሩም፥ እፍረትንም አላወቁም፤ ስለዚህ ከሚወድቁ ጋር ይወድቃሉ፤ በጐበኘኋቸው ጊዜ ይዋረዳሉ፥ ይላል ጌታ።”