ዘፍጥረት 19:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፥ ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋም ጋር ተኛች፥ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያችም ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት፤ ከዚያም ትልቋ ልጁ ሄዳ ከአባቷ ጋራ ተኛች፤ እርሱ ግን ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያን ምሽት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጥተው አሰከሩት፤ ታላቂቱ ልጁም ከእርሱ ጋር ግንኙነት አደረገች። ሎጥ ግን በጣም ሰክሮ ስለ ነበር ስትተኛም ሆነ ስትነሣ አላወቀም። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በዚያችም ሌሊት አባታቸውን ወይን አጠጡት፤ ታላቂቱም ገባች፤ በዚያችም ሌሊት ከአባቷ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛም፥ ስትነሣም አላወቀም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በዚያችም ሌሊት አባታቸውን የወይን ጠጅ አጠጡት ታላቂቱም ገባች፥ ከአባትዋ ጋር ተኛች፤ እርሱም ስትተኛና ስትነሣ አላወቀም። |
በማግስቱም ታላቂቱ ታናሺቱን አለቻት፦ “እነሆ ትናንት ከአባቴ ጋር ተኛሁ፥ ዛሬ ሌሊት ደግሞ የወይን ጠጅ እናጠጣው አንቺም ግቢና ከእርሱ ጋር ተኚ፥ ከአባታችንም ዘር እናስቀር።”