ዘፍጥረት 19:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፦ “አባታችን ሸመገለ፥ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም አንድ ቀን ታላቂቱ ልጅ፣ ታናሺቱን እንዲህ አለቻት፤ “አባታችን አርጅቷል፤ በምድር ሁሉ እንደሚኖሩ ሰዎች ወግ ዐብሮን የሚተኛ ወንድ በአካባቢያችን የለም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አንድ ቀን ታላቂቱ ልጁ እኅትዋን እንዲህ አለቻት፦ “አባታችን ማርጀቱ ነው፤ ልጆች እንድንወልድ እኛን የሚያገቡ ወንዶች በዙሪያችን የሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፥ “አባታችን ሽማግሌ ነው፤ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው በምድር ላይ የለም። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ታላቂቱም ታናሺቱን አለቻት፤ አባታችን ሸመገለ በምድርም ሁሉ እንዳለው ልማድ ሊገናኘን የሚችል ሰው ከምድር ላይ የለም ነዩ |
በዚያን ዘመን ኔፊሊም በምድር ላይ ነበሩ፥ እና ከዚያም በኋላ የእግዚአብሔር ልጆች የሰውን ሴቶች ልጆች ባገቡ ጊዜ ልጆችን ወለዱላቸው፥ እነርሱም በዱሮ ዘመን፥ ስማቸው የታወቀ፥ ኃያላን ሆኑ።
በዚያን ቀን ሰባት ሴቶች አንዱን ወንድ ይዘው፤ “የራሳችንን ምግብ እንበላለን፤ የራሳችንንም ልብስ እንለብሳለን፤ በአንተ ስም ብቻ እንጠራና፤ ውርደታችንን አስቀርልን” ይሉታል።
“ወንድማማቾች በአንድነት ቢኖሩና ከእነርሱ አንዱ ወንድ ልጅ ሳይወልድ ቢሞት፥ የሟቹ ሚስት ከቤተሰቡ ውጭ ባል ማግባት የለባትም። የባሏ ወንድም ይውሰዳትና ያግባት፤ የዋርሳነት ግዴታውንም ይፈጽምላት።