ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም፦ ተነሡ፥ ከዚህ ስፍራ ውጡ፥ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። አማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
ዘፍጥረት 19:15 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፦ “ተነሣ፥ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፥ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሲነጋጋም መላእክቱ ሎጥን፣ “ከከተማዪቱ ጋራ ዐብራችሁ እንዳትጠፉ፣ ሚስትህንና ሁለቱን ሴት ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ቦታ በፍጥነት ውጣ” ብለው አቻኰሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በማግስቱ ጠዋት በማለዳ መላእክቱ ሎጥን “ፍጠን! ከተማይቱ ስትጠፋ አብራችሁ እንዳትጠፉ ሚስትህንና ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ይዘህ ከዚህ ውጣ” እያሉ አጣደፉት። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ “ተነሣ፤ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውሰድ፤ አንተም በከተማዪቱ ሰዎች ኀጢአት እንዳትጠፋ” እያሉ ያስቸኩሉት ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ጎህም በቀደደ ጊዜ መላእክት ሎጥን፥ ተነሣ ሚስትህንና ከዚህ ያሉትን ሁለቱን ሴቶች ልጆችህን ውስድ በከተማይቱ ኃጢአት እንዳትጠፉ እያሉ ያስቸኵሉት ነበር። |
ሎጥም ወጣ፥ ልጆቹን ለሚያገቡት ለአማቾቹም ነገራቸው፥ አላቸውም፦ ተነሡ፥ ከዚህ ስፍራ ውጡ፥ እግዚአብሔር ይህችን ከተማ ያጠፋልና። አማቾቹ ግን የሚያፌዝባቸው መሰላቸው።
እርሱም በዘገየ ጊዜ እግዚአብሔር ስላዘነለት እነዚያ ሰዎች የእርሱን እጅ የሚስቱንም እጅ የሁለቱን የሴቶች ልጆቹንም እጅ ይዘው አወጡትና በከተማይቱ ውጭ አስቀመጡት።
ወደ ሜዳም ካወጡአቸው በኋላ እንዲህ አሉት፦ “ራስህን አድን፥ ወደ ኋላህ አትይ፥ በዚህም ዙሪያ ሁሉ አትቁም እንዳትጠፋም ወደ ተራራው ሸሽተህ አምልጥ።”
እርሱ፥ “በተወደደ ሰዓት ሰማሁህ፤ በመዳንም ቀን ረዳሁህ፤” ይላልና፤ እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ እነሆ፥ የመዳንም ቀን አሁን ነው።