ዘፍጥረት 10:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነርሱ የኖሩበት ግዛት በስተ ምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። አዲሱ መደበኛ ትርጒም መኖሪያ ስፍራቸውም እስከ ሶፋር ድረስ ይዘልቃል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እነርሱ የኖሩበት ምድር በስተምሥራቅ ባለው በተራራማው አገር ከሜሻ እስከ ሰፋር ይደርስ ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ስፍራቸውም ከማሲ አንስቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ስፍራቸውም ከማሴ አንሥቶ ወደ ስፋር ሲል እስከ ምሥራቅ ተራራ ድረስ ነው። |
በለዓምም ምሳሌውን ይመስል ጀመር፥ እንዲህም አለ፦ “ባላቅ ከአራም አመጣኝ፥ የሞዓብ ንጉሥ ከምሥራቅ ተራሮች፤ ‘ና፥ ያዕቆብን ርገምልኝ፤ ና፥ እስራኤልን አውግዝልኝ አለኝ።’