ገላትያ 5:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከመሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የክርስቶስ ኢየሱስ የሆኑት ሥጋን ከክፉ ምኞቱና መሻቱ ጋራ ሰቅለውታል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የኢየሱስ ክርስቶስ የሆኑት ሰዎች ሥጋን ከፍትወቱና ከምኞቱ ጋር ሰቅለውታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ግን ሰውነታቸውን ከምኞትና ከኀጢአት ለዩ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የክርስቶስ ኢየሱስም የሆኑቱ ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ። |
እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ የሚኖር ከሆነ፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። ነገር ግን ማንም የክርስቶስ መንፈስ ከሌለው፥ እርሱ የክርስቶስ አይደለም።
“ምግብ ለሆድ ነው፤ ሆድም ለምግብ ነው፤” እግዚአብሔር ግን ይህንም ያንም ያጠፋቸዋል። ሰውነት ግን ለጌታ ነው እንጂ ለዝሙት አይደለም፤ ጌታም ለሰውነት ነው፤
በፊታችሁ ያለውን ተመልከቱ። ማንም የክርስቶስ መሆኑን ተረድቶ ከሆነ፥ እርሱ የክርስቶስ እንደሆነ እኛም የክርስቶስ መሆናችንን እንዳይዘነጋ።
ክርስቶስ በእኔ ይኖራል እንጂ ከእንግዲህ ወዲያ እኔ አልኖርም፤ አሁን በሥጋ የምኖረው በወደደኝና ስለ እኔ ራሱን በሰጠው በእግዚአብሔር ልጅ ላይ በማመን የምኖረው ነው።
ይህ የሆነው፥ አሕዛብ አብረው እንዲወርሱ፥ በአንድ አካልም አብረው እንዲሆኑ፥ በወንጌልም አማካኝነት በክርስቶስ ኢየሱስ የሆነውን የተስፋ ቃል አብረው እንዲካፈሉ ነው።