ገላትያ 5:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን ይመኛል፥ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚቀዋወሙ የምትፈልጉትን ማድረግ አትችሉም። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሥጋ መንፈስ የማይፈልገውን፣ መንፈስም ሥጋ የማይፈልገውን ይመኛልና፤ እነዚህ እርስ በርሳቸው ስለሚጋጩ፣ የምትፈልጉትን አታደርጉም። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የሥጋ ምኞት ከመንፈስ ምኞት ጋር ይቃረናል፤ መንፈስና ሥጋ እርስ በእርሳቸው ይቃረናሉ፤ ስለዚህ እናንተ የምትፈልጉትን ማድረግ አትችሉም፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሥጋ መንፈስ የማይሻውን ይሻልና፥ መንፈስም ሥጋ የማይሻውን ይሻልና፥ የምትሹትንም እንዳታደርጉ እርስ በርሳቸው ይጣላሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሥጋ በመንፈስ ላይ መንፈስም በሥጋ ላይ ይመኛልና፥ እነዚህም እርስ በርሳቸው ይቀዋወማሉ፤ ስለዚህም የምትወዱትን ልታደርጉ አትችሉም። |
እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።
ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “የዮና ልጅ ስምዖን ሆይ! የተባረክህ ነህ! በሰማያት ያለው አባቴ እንጂ ሥጋና ደም ይህን አልገለጠልህምና።
እንግዲህ ሕግ የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃል ይቃወማልን? በጭራሽ አይደለም። ሕይወትን ሊሰጥ የሚችል ሕግ ተሰጥቶ ቢሆን ኖሮ በእርግጥ ጽድቅ በሕግ በኩል በሆነ ነበር፤