ገላትያ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኛም ደግሞ ሕፃናት በነበርንበት ጊዜ ከዓለም የመጀመሪያ ትምህርቶች ሥር ተገዝተን ነበር፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኛም እንዲሁ ገና ልጆች በነበርንበት ጊዜ፣ ከዓለም መሠረታዊ መንፈሳዊ ኀይሎች ሥር በመሆን በባርነት ተገዝተን ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም እኛ በመንፈሳዊ ነገር እንደ ሕፃናት በነበርንበት ጊዜ ለዚህ ዓለም ሥርዓት ተገዢዎች ሆነን ባሪያዎች ነበርን። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲሁ እኛም ሕፃናት በነበርን ጊዜ፥ ለዚህ ዓለም ስሕተት ተገዝተን ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲሁ እኛ ደግሞ ሕፃናት ሆነን ሳለን ከዓለም መጀመሪያ ትምህርት በታች ተገዝተን ባሪያዎች ነበርን፤ |
እንደገና የፍርሃት ባርያ የሚያደርጋችሁን መንፈስ አልተቀበላችሁምና፥ ነገር ግን “አባ! አባት!” ብለን የምንጠራበትን የልጅነት መንፈስ ተቀብላችኋል።
አሁን ግን እግዚአብሔርን አውቃችሁ ይልቁንም በእግዚአብሔር ታውቃችሁ፥ እንደገና ወደ ደካማና ወደ ተናቀ የመጀመሪያ ትምህርቶች ዳግም ልትገዙላቸው ፈልጋችሁ እንዴት ትመለሳላችሁ?
ከመሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ ርቃችሁ ከክርስቶስ ጋር ከሞታችሁ፥ ከዓለም እንዳልተለያችሁ ዓይነት ኑሮ ለምን ትኖራላችሁ? ለምንስ እንደነዚህ ላሉት ትእዛዞች ትገዛላችሁ?
እንደ ክርስቶስ ትምህርት ሳይሆን እንደ ሰው ወግና እንደ መሠረታዊው የዓለም ረቂቅ መንፈስ በፍልስፍናና በከንቱ መታለል ማንም እንዳይማርካችሁ ተጠንቀቁ።
እስከ አሁን በነበረው ጊዜ አስተማሪዎች ልትሆኑ ሲገባችሁ፥ እንደገና የእግዚአብሔር ቃላት የመጀመሪያውን ትምህርት እንዲያስተምራችሁ ሰው ያስፈልጋችኋልና፤ የሚያስፈልጋችሁም ወተት ነው እንጂ ጠንካራ ምግብ አይደለም።