ሕዝቅኤል 9:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነሆም በፍታ የለበሰው፥ የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው፦ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ ብሎ በቃሉ መለሰ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነሆ በፍታ የለበሰውና በጐኑም የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር ያነገበው ሰው ተመልሶ፣ “እንዳዘዝኸው ፈጽሜአለሁ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ያ በፍታ የለበሰውና የጽሕፈት ዕቃ ማኅደር የያዘው ሰው ተመልሶ መጥቶ “ያዘዝከኝን ሁሉ ፈጽሜአለሁ” ብሎ ለእግዚአብሔር ተናገረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነሆም በፍታ የለበሰው፥ የሰንፔር መታጠቂያም በወገቡ የታጠቀው ሰው መጣ፥ “ያዘዝኸኝንም አድርጌአለሁ” ብሎ በቃሉ መለሰ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነሆም፥ በፍታ የለበሰው የቀለም ቀንድም በወገቡ የያዘው ሰው፦ ያዘዝኸኝን አድርጌአለሁ ብሎ በቃሉ መለሰ። |
እነሆ ስድስት ሰዎች ወደ ሰሜን ከሚመለከተው ከላይኛው በር መንገድ መጡ፥ እያንዳንዱም አጥፊውን መሣሪያ በእጁ ይዞ ነበር፥ በመካከላቸውም የበፍታ ልብስ የለበሰ፥ የጸሐፊ የቀለም ቀንድ በወገቡ የያዘ አንድ ሰው ነበረ። እነርሱም ገብተው በናሱ መሠዊያ አጠገብ ቆሙ።
የመጀመሪያውም መልአክ ሄዶ ጽዋውን በምድር ላይ አፈሰሰ፤ የአውሬውም ምልክት ባለባቸው ለምስሉም በሚሰግዱ ሰዎች ላይ ክፉኛ የሚነዘንዝ ቁስል ሆነባቸው።