ጭንቀት መጥቷል፥ ሰላምም ይሻሉ፥ አይገኝምም።
ሽብር በመጣ ጊዜ ሰላምን ይሻሉ፤ ነገር ግን አያገኟትም።
ጭንቀት በሚመጣበት ጊዜ ሰላምን ትሻላችሁ፤ ነገር ግን አታገኙም፤
ጥፋት መጥቶአል፤ ሰላምም ይሻሉ፤ እርሱም አይገኝም።
ጥፋት መጥቶአል፥ ሰላምም ይሻሉ እርሱም አይገኝም።
ለክፉዎች ሰላም የላቸውም ይላል አምላኬ።
ምክንያቱም ሰላም ሳይኖር ሰላም እያሉ ሕዝቤን አታልለዋልና፥ አንድ ሰው ቅጥር ሲሠራ፥ እነሆ በኖራ ይቀቡታል፤
እነርሱም ስለ ኢየሩሳሌም ትንቢት የተናገሩ፥ ሰላም ሳይኖር የሰላምን ራእይ ያዩላት የእስራኤል ነቢያት ናቸው፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።
በማሮት የምትቀመጠው መልካም ነገርን ትጠባበቃለችና፤ ነገር ግን ክፉ ነገር ከጌታ እስከ ኢየሩሳሌም በር ድረስ ወርዶአል።