ለከተማይቱ ይዞታ በተቀደሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠገብ ወርዱ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ የሆነውን ስፍራ ታደርጋላችሁ። እርሱም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል።
ሕዝቅኤል 48:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በተቀደሰው መባ አጠገብ የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ ዐሥር ሺህ ወደ ምዕራብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ይህም በተቀደሰው መባ አጠገብ ይሆናል። ምርቷም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚህ የሚቀረው፣ የተቀደሰውን ክፍል የሚያዋስነውና በተጓዳኝ ያለው ቦታ በምሥራቅ ዐሥር ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። ምርቱም ለከተማዪቱ ሠራተኞች ምግብ ይሆናል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከተቀደሰው ክልል በምሥራቅ ዐሥር ሺህ ክንድ በምዕራብ ዐሥር ሺህ ክንድ ተነሥቶለት ከተማይቱ ከተሠራች በኋላ የሚቀረው ትርፍ ቦታ በከተማይቱ ለሚኖሩት ሕዝብ የእርሻ መሬት ይሆናል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) “በተቀደሰው መባ አንጻር የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ ዐሥር ሺህ፥ ወደ ምዕራብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። በተቀደሰው መባ አንጻር ይሆናል። ፍሬውም ከተማዪቱን ለሚያገለግሉ መብል ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በተቀደሰው መባ አንጻር የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ አሥር ሺህ ወደ ምዕራብም አሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። በተቀደሰው መባ አንጻር ይሆናል። ፍሬውም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል። |
ለከተማይቱ ይዞታ በተቀደሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠገብ ወርዱ አምስት ሺህ ክንድ ርዝመቱም ሀያ አምስት ሺህ ክንድ የሆነውን ስፍራ ታደርጋላችሁ። እርሱም ለእስራኤል ቤት ሁሉ ይሆናል።
ከተማይቱ ማሰማርያ ይኖራታል፤ በሰሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደቡብ በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምሥራቅ በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በምዕራብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆናል።