Biblia Todo Logo
La Biblia Online

- Anuncios -




ሕዝቅኤል 48:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

18 “በተ​ቀ​ደ​ሰው መባ አን​ጻር የተ​ረ​ፈው ርዝ​መቱ ወደ ምሥ​ራቅ ዐሥር ሺህ፥ ወደ ምዕ​ራ​ብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆ​ናል። በተ​ቀ​ደ​ሰው መባ አን​ጻር ይሆ​ናል። ፍሬ​ውም ከተ​ማ​ዪ​ቱን ለሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ መብል ይሆ​ናል።

Ver Capítulo Copiar

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

18 ከዚህ የሚቀረው፣ የተቀደሰውን ክፍል የሚያዋስነውና በተጓዳኝ ያለው ቦታ በምሥራቅ ዐሥር ሺሕ ክንድ፣ በምዕራብ ዐሥር ሺሕ ክንድ ይሆናል። ምርቱም ለከተማዪቱ ሠራተኞች ምግብ ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

18 በተቀደሰው መባ አጠገብ የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ ዐሥር ሺህ ወደ ምዕራብም ዐሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። ይህም በተቀደሰው መባ አጠገብ ይሆናል። ምርቷም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

18 ከተቀደሰው ክልል በምሥራቅ ዐሥር ሺህ ክንድ በምዕራብ ዐሥር ሺህ ክንድ ተነሥቶለት ከተማይቱ ከተሠራች በኋላ የሚቀረው ትርፍ ቦታ በከተማይቱ ለሚኖሩት ሕዝብ የእርሻ መሬት ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

18 በተቀደሰው መባ አንጻር የተረፈው ርዝመቱ ወደ ምሥራቅ አሥር ሺህ ወደ ምዕራብም አሥር ሺህ ክንድ ይሆናል። በተቀደሰው መባ አንጻር ይሆናል። ፍሬውም ከተማይቱን ለሚያገለግሉ ለመብል ይሆናል።

Ver Capítulo Copiar




ሕዝቅኤል 48:18
6 Referencias Cruzadas  

“ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ይዞታ በተ​ቀ​ደ​ሰው የዕጣ ክፍል መባ አጠ​ገብ ወርዱ አም​ስት ሺህ፥ ርዝ​መ​ቱም ሃያ አም​ስት ሺህ የሆ​ነ​ውን ስፍራ ታደ​ር​ጋ​ላ​ችሁ። እር​ሱም ለእ​ስ​ራ​ኤል ቤት ሁሉ ይሆ​ናል።


ለከ​ተ​ማ​ዪ​ቱም ማሰ​ማ​ርያ ይኖ​ራ​ታል፤ በሰ​ሜን በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በደ​ቡ​ብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በም​ሥ​ራ​ቅም በኩል ሁለት መቶ አምሳ፥ በም​ዕ​ራ​ብም በኩል ሁለት መቶ አምሳ ክንድ ይሆ​ናል።


ከእ​ስ​ራ​ኤል ነገድ ሁሉ ከተ​ማ​ዪ​ቱን የሚ​ያ​ገ​ለ​ግሉ ያር​ሱ​ታል።


በዚ​ያም ቀን ኢያሱ እነ​ር​ሱን ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ እን​ጨት ቈራ​ጮ​ችና ውኃ ቀጂ​ዎች አደ​ረ​ጋ​ቸው። ስለ​ዚ​ህም የገ​ባ​ዖን ሰዎች ለማ​ኅ​በ​ሩና ለእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር መሠ​ዊያ፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርም ለመ​ረ​ጠው ስፍራ እስከ ዛሬ ድረስ እን​ጨት ቈራ​ጮች፥ ውኃም ቀጂ​ዎች ሆኑ።


Síguenos en:

Anuncios


Anuncios