ሕዝቅኤል 43:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለኃጢአት መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ ከመቅደሱ ውጭ ባለው ቤት በተወሰነው ስፍራ ይቃጠላል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይፈኑን ስለ ኀጢአት መሥዋዕት ወስደህ፣ በቤተ መቅደሱ አካባቢ ከመቅደሱ ውጩ ለዚሁ ተብሎ በተመደበው ስፍራ ታቃጥለዋለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለኃጢአት ስርየት መሥዋዕት ሆኖ የቀረበውንም ኰርማ ወስደህ ለቤተ መቅደሱ ከተከለለው የተቀደሰ ቦታ ውጪ ለዚህ በተወሰነው ስፍራ ታቃጥለዋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለኀጢአትም መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፤ በመቅደሱም ውጭ በቤቱ በተለየው ስፍራ ይቃጠላል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ለኃጢአትም መሥዋዕት የሚሆነውን ወይፈን ትወስዳለህ፥ በመቅደሱም ውጭ በቤቱ በታዘዘው ስፍራ ይቃጠላል። |
ወይፈኑን ሁሉ ከሰፈሩ ውጭ አመድ ወደሚፈስበት ወደ ንጹሕ ስፍራ ይወስዳል፥ በእንጨትም ላይ በእሳት ያቃጥለዋል፤ አመድ በሚፈስስበት ስፍራ ይቃጠላል።