ሕዝቅኤል 41:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመሬት አንሥቶ እስከ መግቢያው ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር። የመቅደሱም ግንብ እንደዚህ ነበረ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከወለሉ አንሥቶ ከመግቢያው በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ፣ የውስጡ መቅደስ የውጭ ግድግዳ ላይ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፍ ተቀርጿል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከወለሉ አንሥቶ ከበሮቹ በላይ እስካለው ስፍራ ድረስ በግድግዳዎቹ ላይ የኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ቅርጽ ተቀርጸው ነበር። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመሬት አንሥቶ እስከ ደጁ ራስ ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር፤ የመቅደሱ ግንብ እንደዚህ ነበረ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመሬት አንሥቶ እስከ ደጁ ራስ ድረስ ኪሩቤልና የዘንባባ ዛፎች ተቀርጸው ነበር። የመቅደሱ ግንብ እንደዚህ ነበረ። |
“እኔ ጌታ አምላካችሁ ነኝና ለራሳችሁ ይሆኑ ዘንድ ጣዖታትን አትሥሩ፥ የተቀረጸም ምስል ወይም ሐውልት አታቁሙ፤ ለእርሱም ለመስገድ በምድራችሁ ላይ የተቀረጸ ድንጋይ አታኑሩ።